አርዕስተ ዜና

ፊፋ የዓለም ዋንጫ ተሳታፊ አገራትን ቁጥር ወደ 48 አሳደገ

10 Jan 2017
572 times

አዲስ አበባ ጥር 2/2009 የዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (ፊፋ) የዓለም ዋንጫ ተሳታፊ አገራትን ቁጥር ከ 32 ወደ 48 ከፍ እንዲል ወሰነ።

ውሳኔው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ 2026 የዓለም ዋንጫ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል።

ሴፕ ብላተርን በመተካት በየካቲት 2008 ዓ.ም የፊፋ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት ጂያኒ ኢንፋቲኖ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት በዓለም ዋንጫ የሚሳተፉ አገራት ቁጥርን እንደሚያሳድጉ ቃል መግባታቸው ይታወሳል።

ይህን ሀሳባቸው ለፊፋ ምክር ቤት አባላት አቅርበው ዙሪክ በሚገጸው የማህበሩ ዋና ጽህፈት ቤት በሙሉ ድምጽ ማጸደቅ ችለዋል።

በዚህም 48ቱ አገራት በ 16 ምድብ ተደልድለው በየምድቡ ሦስት ሦስት አገራት እንዲመደቡ ይደረጋል።

የተሳታፊ አገራት ቁጥር ማደጉን ተከትሎ በዓለም ዋንጫ የጨዋታዎች ቁጥር ከ 64 ወደ 80 ከፍ ያለ ሲሆን ውድድሩም በ 32 ቀናት ውስጥ የሚጠናቀቅ ይሆናል።

ፊፋ የተሳታፊ አገራት ቁጥር ሲያሳድግ ከ 1998 በኋላ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

የተሳታፊ አገራት ቁጥር ማደጉን ተከትሎ የአውሮፓ አገራት ቁጥራቸውን ከ 13 ወደ 16 ከፍ ብሏል።

የአፍሪካ ከ 5 ወደ 9፣ የእስያ ከ 4 ነጥብ 5 ወደ 8 ነጥብ 5፣ የደቡብ አሜሪካ ከ 4 ነጥብ 5 ወደ 6 ፣ የምዕራብና መካከለኛ አሜሪካና ካርቢያን አገራት ኮንፌዴሬሸን (ኮንካፍ) ከ 3 ነጥብ 5 ወደ 6 ነጥብ 5፣ ኦሽንያ ከዜሮ ነጥብ አምስት ወደ አንድ እንዲሁም አስተናጋጅ አገር ሊሆን እንደሚችል ተመልክቷል።

በነጥብ የተቀመጠው የእስያና የደቡብ አሜሪካ እንዲሁም የኮንካፍ አገራት ቁጥሩ ሊቀንስ አሊያም ሊጨምርም እንደሚችል ተጠቁሟል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ