አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

የወልዲያ ስታዲየም በመጪው ጥር ይመረቃል

21 Dec 2016
1283 times

አዲስ አበባ ታህሳስ 12/2009 በሼህ ሙሐመድ ሁሴን አልአሙዲ ወጪ የተገነባው ዘመናዊው የወልዲያ ስታዲየም በመጪው ጥር እንደሚመረቅ ተገለጸ።

ባለሃብቱ ስታዲየሙን ያስገነቡት በከተማው አስተዳደርና ነዋሪው በተዘጋጀ የስታዲየሙ ግንባታ የገቢ ማሳባሰቢያ ላይ በእንግድነት ተገኝተው የህዝቡን ፍላጎትና ምኞት በማየታቸው የግንባታውን ሙሉ ወጪ ችለው ለማስገንባት በገቡት ቃል መሰረት ነው።

በሜድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ የተገነባው ይህ ስታዲየም 25 ሺህ 155 ሰዎችን በወንበር የመያዝ አቅም ሲኖረው ለግንባታው ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተድርጎበታል።

በወልዲያ ከተማ የተገነባው ስታዲየም የአሎምፒክ ውድድርን የማስተናግድ አቅም ያለው መዋኛ ገንዳ፣ የቅርጫት ኳስ ሜዳ፣ የእጅ ኳስ፣ የመረብ ኳስና የቴኒስ መጨዋቻዎችንም ያካተተ ነው።

ግንባታውን ለማጠናቀቅ አራት አመት ተኩል ፈጅቷል።

የሜድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ፕሬዝዳንት ዶክተር አረጋ ይርዳው "በግንባታው ደረጃቸውን የጠበቁ ስታዲየሞች መስራት የሚችሉ ወጣት ባለሙያዎችን አፍርተናል" ብለዋል።

95 በመቶ ያህል የግንባታው ቁሶች በአገር ውስጥ የተሸፈኑ ሲሆን በሰው ኃይል በኩልም ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ ባለሙያዎች መገንባቱ ተገልጿል።

ስታዲየሙን ባለሃብቱ ያስገንቡት እንጂ ንብረትነቱ የወልዲያ ከተማ አስተዳደርና ህዝብ ሲሆን ከስታዲየሙ የሚገኝ ማንኛውም ጥቅም ሙሉ በሙሉ ለከተማው አስተዳደርና ለህዝቡ የሚውል ይሆናል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ