አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ 798 ሰልጣኞችን አስመረቀ

30 Jul 2016
1571 times

አዲስ አበባ ሀምሌ 23/2008 ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ለ33ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 798 ሰልጣኞችን ዛሬ አስመረቀ።        

ዩኒቨርሲቲው በኢትዮጵያ የመጀመሪያ በሆነው በማዕድን ምህንድስና 17 ሰልጣኞችን  አስመርቋል።

አካውንቲንግ፣ኢኮኖሚክስ፣ኮምፒዩተር ሳይንስ፣ሲቪል ምህንድስናና የቢዝነስ አስተዳደር ምረቃ ከተካሄደባቸው የሥልጠና መርሃ ግብሮች  መካከል ይጠቀሳሉ።

ከተመራቂዎቹ ውስጥ 105 ቱ በድህረ ምረቃ መርሃ ግብር ትምህርታቸውን መከታተላቸውንና ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ መካከል 48ቱ ሴቶች መሆናቸውን በሚሊኒየም አዳራሽ በተከናወነው የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገልጿል።

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሼህ መሐመድ ዓሊ አል አሙዲ በበኩላቸው አገሪቱ እያስመዘገበች ያለችውን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የሚመጥን የተማረ የሰው ኃይል እንደሚያስፈልጋት ተናግረዋል። 

ተመራቂዎችም የቀሰሙትን ዕውቀት ወደ ተግባር በመቀየር የአገሪቱን የልማት አቅጣጫ በመደገፍ ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።                                                  

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አረጋ ይርዳው በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ከብዛት ይልቅ ጥራት ላይ አተኩሮ  እየሰራ ነው ብለዋል።  

''ትምህርት መጨረሻ የለውም። ተመራቂ ተማሪዎች በርትተው በትምህርቱ መግፋት አለባቸው'' ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።  

የዩኒቨርሲቲው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ብርሃኑ ሲሳይ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር፣በጥናትና ምርምር እንዲሁም ኀብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ጥረቱን አጠናክሯል።

''በተለይ ለአገር ግንባታ ወሳኝ ተብለው የተለዩ ዘርፎች በመለየት የሚሰጠውን የትምህርት ዓይነት እያሳደገ መጥቷል'' ብለዋል። 

በዚሁ መሠረት በእንስሳት እርባታና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በአትክልትና ፍራፍሬ ምርትና ቴክኖሎጂ የትምህርት ዘርፎች በሚቀጥለው ዓመት ለመጀመር መዘጋጀቱን ተናግረዋል። 

ዩኒቨርሲቲው በአገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በማዕድን ምህንድስና ዘርፍ ለአምስት ዓመታት ያሰለጠናቸውን 17 ባለሙያዎችንም አስመርቋል። 

ዩኒቨርሲቲው በአሁኑ ወቅት በስድስት የድህረ ምረቃና 13 የቅድመ ምረቃ የትምህርት ዘርፎች ሥልጠና እየሰጠ ሲሆን የተመሰረተው በ1991 ነው።

 

  

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ