አርዕስተ ዜና

የመድኃኒት ፋብሪካ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ግንባታ እያተካሄደ መሆኑ ተገለጸ

352 times

መቀሌ 6/2010  በአዲግራት ከተማ የሚገኘው አዲስ መድኃኒት ፋብሪካ የማስፋፊያ ፕሮጀክት በአንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር በጀት ግንባታው እየተካሄደ ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ዳንኤል ገብረ ዮሐንስ ለኢዜአ እንደገለጹት የፋብሪካው የማስፋፊያ ግንባታ እየተካሄደ ያለው "ፊፍቲ ፎር ካፒታል"  ከተባለው የእንግሊዝ ኩባንያ  ጋር በመሆን  ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት መድኃኒት የሚመረትበት  ህንጻ ግንባታ የተጠናቀቀ ሲሆን የህንጻውን ውስጣዊና ውጫዊ ግንባታዎች  የማዘጋጀትና የኤሌክትሮ ሜከኒካል  ስራዎቹ እንደሚቀጥልም አመልክተዋል።

የፋብረካው የማስፋፊያ ስራ  በአንድ ዓመት ከሶስት ወር በኋላ ተጠናቆ ወደ ማምረት ስራው እንደሚገባም አቶ ዳንኤል አስታውቀዋል፡፡

የማስፋፊያ ግንባታው  የነባሩን ፋብሪካ የማምረት አቅም በሶስት እጥፍ እጥፍ ከፍ የሚያደርግ ከመሆኑ  በተጨማሪ ምርቱን ለውጪ ገበያ እንደሚያቀርብም  ስራ አስኪያጁ አስታውቀዋል፡፡

ከአሁን በፊት ያልነበረው  ስምንት አዳዲስ መድኃኒቶችን ያመርታል ተብሎ እንደሚጠበቅም ጠቅሰዋል፡፡

"የፋብሪካው ግንባታ ሲጠናቅ  ለሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ከማግኘት ባለፈ  ለአንድ ሺህ የሚሆኑ ወገኖች ቋሚ የስራ ዕድል ያስገኛል "ብለዋል፡፡

በአዲግራት ከተማ የሚገኘው አዲስ የመድኃኒት ፋብሪካን "ፊፍቲ ፎር ካፒታል" የተባለ የእንግሊዝ ኩባንያ 49 በመቶ ድርሻ ባለፈው ዓመት መግዛቱ ይታወቃል፡፡

 

 

Last modified on Wednesday, 14 February 2018 17:43
Rate this item
(0 votes)

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን