አርዕስተ ዜና

ለ12ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል ስኬታማነት አስተዋጽኦ ላበረከቱ የእውቅና ምስክር ወረቀት ተሰጠ Featured

12 Jan 2018
189 times

ሰመራ ጥር 4 /2010 የአፋር ክልላዊ መንግስት 12ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል በስኬት እንዲጠናቀቅ የጎላ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የእውቅና  ምስክር ወረቀት  ሰጠ።

በሰመራ ከተማ ትላንት በተካሄደ ስነ- ስርአት ላይ የእውቅና ምስክር ወረቀት የተሰጣቸው በክልሉ የሚገኙ አርብቶ አደሮች፣ ነጋዴዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የዘርፍ መስሪያቤቶች ናቸው ።

በተጨማሪም ከክልሉ ውጭ ላሉ ባለሀብቶች፣ የዴደራል ተቋማትና ሚኒስቴር መስሪያቤቶች እውቅናና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷል ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ስዩም አወል በወቅቱ ባደረጉት ንግግር ከበዓሉ ጋር ተያይዞ በአጭር ግዜ ውስጥ በመንግስት የተከናወኑ የመሰረተ-ልማት ሥራዎች የሕብረተሰቡን ዘላቂ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያግዙ ናቸው።

" የልማት ሥራዎቹ በየደረጃው ለሚገኙ የክልሉ አመራሮችና አርብቶ አደሩ ሕብረተሰብ በራስ አቅም መልማት እንደሚቻል በተግባር ያሳዩ ናቸው " ብለዋል።

ከክልሉና ከፌደራል መንግስት በተጨማሪ አርብቶ አደሩ፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ ባለሀብቶች፣ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በዓሉ በስኬትና በደመቀ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የላቀ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

በበዓሉ የታየው የሕዝብና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ የአርብቶ አደሩን ሕይወት በዘላቂነት ሊቀይሩ በሚችሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ሥራዎች ላይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል ።

የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መሀመድ አፍኬኤ በበኩላቸው የ12ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል አስመልከቶ በተለይም በክልሉ ዋና ከተማ በግል የተከናወኑ የኢንቨስትመንትና ሌሎች የልማት ሥራዎች ለቀጣይ እድገት መሰረት የጣሉ መሆናቸውን ተናግረዋል ።

የእውቅና ምስክር ወረቀት ከተሰጣቸው የንግዱ ማህበረሰብ አባላት መካከል አቶ አህመዲን ዋሴ በሰጡት አስተያየት እንደ ነዋሪነታቸው ለበአሉ ስኬት አቅማቸው የፈቀደውን ማድረጋቸውን በመግለፅ በቀጣይ ለክልሉ ልማት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል ።

ሌላው በአበአላ ወረዳ የሚኖሩት የሀገር ሽማግሌ ረዳኢ ተካ በበኩላቸው፣ ህዝብን አስተባብሮ ጸጥታን ከማስፈንና እንግዶችን ተቀብሎ ከማስተናገድ አንጻር ለበዓሉ ስከኬት የድርሻቸውን ማበርከታቸውን ተናግረዋል ።

በቀጣይም ለክልሉ ሰላምና ልማት መረጋገጥ ተሳትፏቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል ።

በእውቀና ምስክር ወረቀት አሰጣጥ ስነ ስርአት ላይ ከክልሉ 32 ወረዳዎች የተውጣጡ ከ1ሺህ 500 በላይ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች፣ ባለሀብቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ