አርዕስተ ዜና

በአርባ ምንጭ ለህንፃ ህንባታ የተቆፈረ አፈር ተደርምሶ የአስር ሰዎች ህይወት አለፈ

03 Jan 2018
324 times

አርባምንጭ ታህሳስ 25/2010 በአርባ ምንጭ ዙሪያ  በሚገኝ  ወረዳ ለአንድ ህንጻ ግንባታ የተቆፈረ አፈር ትላንት ምሽት ተደርምሶ የአስር ስዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

 ህይወታቸው ካለፈው ሌላም በሁለት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱም ተመልክቷል፡፡

 የወረዳው የፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ተወካይ ኢንስፔክተር ሚልኪያስ ኩና ለኢዜአ እንደገለፁት አደጋው የደረሰው በወረዳው ዝጊቲ ባቆሌ በተባለ ቀበሌ ግንባታ ላይ ባለው የኃይማኖት ተቋም  ህንጻ ስራ የተቆፈረ አፈር በመደርመሱ ነው ።

 በጉድጓድ ውስጥ ሆነው አፈር በማውጣት ላይ የነበሩ አስር ሰዎች በናዳው ህይወታቸው ሲያልፍ ሌሎች ከተደረመሰው አፈር ጋር ወደ ጉድጓዱ የገቡ ሁለት ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ።

 የማቾቹ አስከሬን ቤተሰቦቻቸው እንዲረከቡ መደረጉን ያመለከቱት ኢኒስፔክተሩ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ደግሞ በአርባምንጭ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን አስታውቀዋል።

 የመሰረት ግንባታው ከተጠናቀቀው ህንጻ ስር ለፍሳሽ ቆሻሻ ማስተላለፊያ ከተቆፈረ 10 ሜትር ጥልቀት ካለው ጉድጓድ ውስጥ የወጣ አፈር በመደርመሱ አደጋው ሊከሰት እንደቻለ ኢኒስፔክተሩ ገልጸዋል፡፡ 

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ