አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

ለሠራተኞቻቸው የጡረታ አበል ክፍያ የማይፈጽሙ የግል ድርጅቶች እንዳሉ ተገለጸ

14 Nov 2017
567 times

አዲስ አበባ  ህዳር  5/2010 የሠራተኞችን የጡረታ አበል ክፍያ በማይፈጽሙ የግል ድርጅቶች ላይ የሚደረገው ክትትል ዝቅተኛ መሆኑ ተገለጸ።

የግል ድርጅቶች ሰራተኞች ማሕበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ የ2010 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ አመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለህዝብ ክንፍ እና ለኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበር ኮንፌዴሬሽን አቅርቧል።

የሠራተኞቻቸውን የጡረታ አበል ክፍያ የማይፈጽሙ አዲስ የተከፈቱም ሆኑ ነባር ድርጅቶች እንዳሉ በውይይቱ ወቅት ተነስቷል።

ኤጀንሲው ድርጅቶቹ ለሰራተኞቻቸው የጡረታ አበል ክፍያ እንዲፈጽሙ ክትትልና ቁጥጥር ከማድረግ ባለፈ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችንም ማዘጋጀት እንዳለበት ተነግሯል።

በተለይ በማህበር ያልተደራጁ የሸማች ማህበራት እና የትራንስፖርት ተቋማት ሰራተኞች ወደ ጡረታ አቅድ ስርዓት እንዲገቡ በትኩረት መስራት እንዳለበት ተጠቅሷል።

የጡረታ አበል ክፍያ አፈጻጸም ሂደትን ማቀላጠፍ፣የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶችን የትራንስፖርት ችግር መፍታት ኤጀንሲው ትኩረት ያልሰጠባቸው የስራ ክፍሎች መሆናቸውንም ተሳታፊዎቹ አሳስበዋል።

የሰው ሃይል በማሟላት የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ወደ ጡረታ አቅድ እንዲገቡ የማድረጉን ተግባር ኤጀንሲው ማጠናከር እንዳለበትም ተጠቁሟል።

የጡረታ አበል ክፍያ አፈጻጸም ሂደትን ማቀላጠፍ፣የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶችን የትራንስፖርት ችግር መፍታት ኤጀንሲው በትኩረት ሊሰራቸው እንደሚገባ ተሳታፊዎቹ አሳስበዋል።

የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ውቤ ፤ በሩብ ዓመቱ የሥራ አፈጻጸም ከ3 ሺህ በላይ የግል ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ሠራተኞችን በኤጀንሲው ተመዝግበዋል።

ምዝገባ ያካሄዱት የግል ድርጅቶች ምንም ዓይነት የጡረታ አበል ክፍያ ሳይፈጸሙ የቆዩ እና አንዳንድ ድርጅቶች ደግሞ የጡረታ ክፍያውን በሰራተኞች የጡረታ መዝገብ ቁጥር አለማስመዝገባቸውን ምክትል ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም 142 የግል ድርጅቶች ለኤጀንሲው የሠራተኞቻቸውን ጡረታ አቅድ እንዲከፍሉ በተደጋጋሚ ኤጀንሲው ቢያሳውቃቸውም፤ ፈጣን ምላሽ ባለመስጠታቸው በኤጀንሲው የህግ ዳይሬክቶሬት አማካኝነት ወደ ምዝገባ ሂደት እየገቡ መሆኑንም ተገልጿል።

የሰው ሀይል ፍልሰት፣ከግል ድርጅቶች የሚቀርቡ መረጃዎች ያለመሟላት፣የአሠሪ እና ሠራተኛው ግንዛቤ ውስንነት ኤጀንሲው በሩብ አመቱ አፈጻጸም ያጋጠሙት ችግሮች መሆናቸውን በሪፖርቱ ላይ ተጠቁሟል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ