አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

በህገ ወጥ መንገድ ይንቀሳቀሱ ነበር የተባሉ አስር ኮሌጆች እንዲዘጉ ተደረገ

14 Nov 2017
585 times

መቀሌ ህዳር 5/2010 በትግራይ እውቅና ሳይኖራቸውና ፈቃዳቸውን ሳያሳድሱ በህገ ወጥ መንገድ ይንቀሳቀሱ ነበር ያላቸው አስር የግል ኮሌጆች እንዲዘጉ ማድረጉን የክልሉ የቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው  ኃላፊ ዶክተር ሙሉጌታ ሓዱሽ እንዳሉት ኮሌጆቹ ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን የኮሌጅ መግቢያ ነጥብ መመሪያን ጥሰው በህገ ወጥ መንገድ በማሰልጠንና የተሳሳተ የዕውቅና መረጃ ለተማሪዎች በመስጠት ሲያታልሉ ቆይተዋል።

ፈቃዳቸው ሳያሳድሱ ተማሪዎችን ተቀብለው ከመገኘታቸውም ሌላ የማስተማሪያ ክፍሎች ፣  የስልጠና መሳሪያዎችና የሰለጠኑ ባለሙያ ሳይኖራቸውና እውቅና ሳይሰጣቸው ይንቀሳቀሱ ነበር።

በተጨማሪም የትምህር ጥራትን ለማስጠበቅ ከመጣር ይልቅ ገቢ ላይ ብቻ በማትኮር ሲሰሩና በየጊዜው የትምህርት ከፍያን በመጨመር ተማሪዎችን ሲበድሉ መቆየታቸውንም   ኃላፊው ጠቅሰዋል፡፡

ኮሌጆቹ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ተሸሽገው በህገ ወጥ መንገድ ከአንድ እስከ ሶስት ዓመት ይንቀሳቀሱ እንደነበርና እንዲዘጉ የተደረገውም ከሐምሌ 2009 ዓ.ም ወዲህ ነው፡፡

የተማሪዎቹ ዕድል እንዳይበላሽ  ያወጡት ገንዘብ ኮሌጆቹ ሸፍነው ህጋዊ እውቅና ወዳላቸው የትምህርት ተቋማት በማዛወር እንዲያስተምሯቸው እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡

እንዲዘጉ የተደረጉ ኮሌጆች የስራ ኃላፊዎች ስለተወሰደው እርምጃ አስመልክቶ ኢዜአ ባላቸው የስልክ አድራሻ በተደጋጋሚ ለማነጋገር ቢሞከረም ማግኘት አልቻለም፡፡

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ