አርዕስተ ዜና

ለቀብር ይጓዙ የነበሩ 21 ሰዎች በተሽከርካሪ አደጋ ህይወታቸው አለፈ

14 Nov 2017
584 times

መቀሌ ህዳር 5/2010 በትግራይ ምስራቃዊ ዞን በአፅቢ ወንበርታ ወረዳ ለቀብር ይጓዙ የነበሩ 21 ሰዎች ትናንት በደሰረባቸው የተሽከርካሪ አደጋ ህይወታቸው አለፈ፡፡  

አደጋው የደረሰው 34 ተሳፋሪዎችን ጭኖ በመጓዝ ላይ የነበረው ኮድ 3- 01758 ትግ  መለስተኛ አውቶቡስ  በመገልበጡ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል ፡፡

ከተሳፋሪዎቹ መካከል 13ቱ  በትርፍ የተሳፈሩ እንደነበርም ተገልጿል

ተሸከርካሪው ወደ ሳዕሲዕ ፃዕዳ እምባ ወረዳ ለቀብር የሚሄዱ ሰዎችን አድርሶ ሲመለስ አፅቢ ወንበርታ ወረዳ  ልዩ ቦታ አፅገበት የተባለው ስፍራ ሲደርስ በመገልበጡ አደጋው ሊደረስ ችሏል፡፡

የአፅቢ ወንበርታ ወረዳ ትራፊክ ፖሊስ አስተባባሪ ኢንስፔክተር ገብረመድህን ንርአ እንደገለለጹት በአደጋው ሾፌሩን ጨምሮ የ21 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ አልፏል።

እንዲሁም  አምስት ሰዎች ከባድ አንድ ሰው ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው ወደ መቀሌ ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል እና  ውቅሮ ሆስፒታል ተወስደው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑንም አመልክተዋል፡፡ 

አንድ ህፃንና ሌሎቹ ቀሪ ሰዎች የአካል ጉዳት ሳይደርስባቸው መትረፋቸውን ኢንስፔክተሩ ጠቅሰው የሟቾቹ አስክሬን ቤተሰቦቻቸው እንዲረከቡ መደረጉንም አስታውቀዋል፡፡

የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ