አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

በታላቁ መሪ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሕይወት ላይ የሚያጠነጥን 'የዘመን ክስተት' የተሰኘ መፅሃፍ ለንባብ በቃ Featured

13 Aug 2017
888 times

አዲስ አበባ ነሀሴ 6/2009 በታላቁ መሪ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሕይወት ላይ የሚያጠነጥን 'የዘመን ክስተት-መለስ ዜናዊና አዲሲቷ ኢትዮጵያ' የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ በቃ።

በጋዜጠኛ ገብረ ሚካኤል ገብረ መድህን የተጻፈው ይህ መጽሐፍ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ ታላላቅ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል።

መጽሓፉ በ13 ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ልደት ጀምሮ በትግል፣ በአመራርነት የነበራቸውን ሕይወትና ፍልስፍና እንዲሁም ህልፈትን ያስቃኛል።

መጽሐፉን ለማዘጋጀት ስድስት ዓመታት የፈጀ ጥናትና ምርምር ማድረጉን ደራሲው ገልጿል።

ደራሲው "መፅሃፉ መለስ እንደ  አገር መሪና ግለሰብ፣ እንደ አለማቀፋዊ ፖለቲከኛና የአፍሪካ መብት ተማጋች፣እንደ ጻሀፊና ተመራማሪ ምን ይመስል እንደ ነበር ከማብራራት ባሻገር በአገር ውስጥና በአፍሪካ ደረጃ በዘርፉ የፈጠራቸውን ተጽዕኖዎች ይቃኛል "ብሏል።

መጽሐፉ ከአንባቢያን እይታ ሲፈተሽ የራሱ ክፍተት ሊኖር እንደሚችል በመጥቀስ፤ ወደፊት ብዙ ተመራማሪዎች በመለስ አስተሳስብ ዙሪያ እዲመራመሩና ጥናቶችን እንዲያደርጉ  በር ከፋች እንደሚሆን ጠቁሟል።

ለአገራቸው ለደከሙና አስተሳሰባቸውም ዘመናትን ለሚሻገር እንደ መለስ ዜናዊ አይነት መሪዎች ታሪካቸው ተሰንዶ ለትውልድ መተላለፉ ለቀጣይ ትውልድ መማሪያ ነው ሲሉ በምረቃው ወቅት አስተያይት ሰጭዎች ገልጸዋል።

ከነዚህም መካከል የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት የሰላምና የጸጥታ ዘርፍ ዳይሬክተር ኮማንደር አበበ ሙሉነህ እንደሚሉት መጽሐፉ የመለስ አስተምሮ ለቀጣይ አገር መሪዎች መሰረት ሊጥል እንደሚችል ተናግረዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በበኩላቸው አቶ መለስ ዜናዊ የተለየ ስብዕና ባለቤትና ውሳኔ የመስጠት ብቃት ያላቸው መሪ እንደነበሩ ገልጸዋል።

በስራዎቻቸው ላይ የሚያጠነጥን መጽሃፍ ለንባብ መብቃቱም አዲሱ ትውልድ የመለስን ራዕይ ለማሳካት እንደመነሻ ሊሆን እንደሚችል አመልክተዋል።

በ369 ገጾች የተቀነበበው 'የዘመን ክስተት- መለስ ዜናዊ አዲሲቷ ኢትዮጵያ" መጽሐፉ በአንድ መቶ  ብር  ለገበያ ቀርቧል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ