አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

ቡድኑ ለደቡብ ሱዳን ዜጎችና ለጋምቤላ ክልል ነዋሪዎች ነፃ የህክምና አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ገለጸ Featured

19 Jun 2017
535 times

አዲስ አበባ ሰኔ 12/2009 በጦርነት ለተፈናቀሉ የደቡብ ሱዳን ዜጎችና ለጋምቤላ ክልል ነዋሪዎች ነፃ የህክምና አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን ገለጸ።

ነገ በጋምቤላ የሚከበረውን የዓለም ስደተኞች ቀን አስመልከቶ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ላለፉት ሁለት ዓመታት በጋምቤላ ክልል ተጠልለው ለሚገኙ ስደተኞችና ለክልሉ ህዝብ ነፃ የህክምና እርዳታ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

ድርጅቱ ባለፈው ዓመት ብቻ በጋምቤላ ክልል ኩሌ፣ ፑኒዶ እና ቲርኪዲ የስደተኞች ጣቢያ ባቋቋማቸው የጤና ኬላዎችና ጤና ጣቢያዎች አማካኝነት ከ260 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ስደተኞችና የአካባቢው ነዋሪ የህክምና አገልግሎት መስጠቱን አስታውሷል፡፡

በምስራቅ አፍሪካ የተንሰራፋውን ግጭትና ረሃብ የሸሹ ከ838 ሺህ በላይ ስደተኞች በኢትዮጵያ ተጠልለው ይኖራሉ ያለው የድርጀቱ መግለጫ  በእርስ በርስ ጦርነት እየታመሰች ካለችው ደቡብ ሱዳን ለሚሰደዱና ለአገሪቱ ዜጎች ትኩረት መስጠቱን አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር ደቡብ ሱዳናዊያኑ ስደተኞች በሚገኙባቸው መጠለያ ጣቢያዎችና በጋምቤላ ከተማ ሪፈራል ሆስፒታል ነፃ የህክምና ድጋፍ እየሰጠ መሆኑንም ጠቁሟል።

በስደተኛ ጣቢያዎቹ የሚንቀሳቀሱት የህክምና ቡድኑ አባላት ባለፉት አምስት ወራት ከ600 በላይ ለሚሆኑ ደቡብ ሱዳናዊያን ስደተኞች እና የአካባቢው ነዋሪ እናቶች የማዋለድ አገልግሎት በነፃ መስጠቱንም አመልክቷል።

ቡድኑ ስደተኞቹ በተጠለሉባቸው ጣቢያዎች በተቋቋሙ የጤና ተቋማት እና በጋምቤላ ክልል ከተማ በሚገኘው ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ የህክምና ድጋፍ ይሰጣል፡፡

ወባ ፣ ስር የሰደደ የተመጣጠነ ምግብ እጥረትና የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽን በጣቢያዎቹ በሚገኙት ደቡብ ሱዳናዊያን ዘንድ የሚታዩ ዋና ዋና የጤና ችግሮች ናቸው፡፡

በአሁኑ ወቅት የደቡብ ሱዳን ሁኔታ ተስፋ አስቆራጭ እየሆነ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የጋምቤላ ክልል አሁንም ጦርነቱን የሚሸሹ የደቡብ ሱዳናዊያን መዳረሻ ሆና ቀጥላለች፡፡

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ