አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

ሩዋንዳ የክፍለ-አህጉሩን ዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት ጉባኤ ታስተናግዳለች

19 Jun 2017
308 times

አዲስ አበባ ሰኔ 12/2009 ሩዋንዳ አምስተኛውን የምስራቅ አፍሪካ ዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት ጉባኤ ታስተናግዳለች።

ጉባኤውን የኪጋሊ የግልግል ዳኝነት ማዕከል ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚያስተናግዱ የአፍሪካ የኢኮኖሚ አማካሪ ተቋም ጂ ቢ ኤስ አፍሪካ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

የግልግል ዳኝነት ሰዎች ወይም ተቋማት ያለባቸውን ሙግት (ውዝግብ) ከመደበኛው የፍርድ ስርአት ውጪ ሌላ ሶስተኛ አካል እንዲፈታላቸው የሚያደርጉበት አማራጭ የሙግት መፍቻ ዘዴ ነው።

እነዚህ አካላት ተስማምተው ውሳኔ እንዲወሰንላቸው የመረጡት አካል ብይን የመጨረሻና የማይቀለበሱ ናቸው።

ጉባኤው "ዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት እና የአፍሪካ ኢኮኖሚ ያላቸው ትስስር" በሚል መሪ ቃል ከሶስት ወራት በኋላ በሩዋንዳ መዲና ኪጋሊ ይካሄዳል።

በጉባኤው የዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት በኢኮኖሚ ላይ ያለው ተጽእኖ ዙሪያና የግልግል ዳኝነት ስርዓት በምስራቅ አፍሪካ ያለበትን ደረጃ በመቃኘት የግልግል ዳኝነት ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ይመክራል።

የግልግል ዳኝነት በኢኮኖሚ ላይ ያለውን ተጽዕኖ ጉባኤው በጥልቀት እንደሚዳስስ የሚጠበቅ ሲሆን በምስራቅ አፍሪካ የፍርድ ስርዓቱን አስመልክቶ ባሉ ጅምሮች ዙርያም በሰፊው ይመከራል ተብሏል።

እንዲሁም የዘርፉ ባለሙያዎች የዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት ስርዓት በምስራቅ አፍሪካ አሁን ያለበት ደረጃና የፍርድ ስርዓቱ በአፍሪካ ያሉ ሙግቶችን በመፍታት ረገድ ያለው ፋይዳ ላይ ገለጻ ይደረግበታል።

በኬኒያ፣ በሩዋንዳና ሞሪሽየስ የተቋቋሙ የግልግል ዳኝነት ማዕከላትና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቋቋሙ ማዕከላት ሙግቶችን በመፍታት ረገድ ያላቸው ተሞክሮም በጉባኤው ይቀርባል።

የኪጋሊ የግልግል ዳኝነት ማዕከል ውሳኔ የሚሹ 52 ጉዳዮችን ይዞ በመከታተል ላይ ይገኛል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ