ህገ ወጥ የሆነ 2 ሺህ 200 ጀሪካን የምግብ ዘይት በአዳማ ከተማ ተያዘ

19 Jun 2017
462 times

አዳማ ሰኔ 12/2009 ለድርቅ ተጎጂዎች ከጅቡቲ ወደ  ሀገር ውስጥ የገባ 2 ሺህ 200 ጀሪካን የምግብ ዘይት በህገ ወጥ መንገድ አዳማ ከተማ  ሲራገፍ መያዙን ፖሊስ  አስታወቀ።

የአዳማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ  የህዝብ ግንኙነት ዲቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ዲኖ ኢማም ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የምግብ ዘይት  የተያዘው ትናንት ምሽት  5 ሰዓት ተኩል አካባቢ አዳማ ከተማ ቀበሌ ዜሮ አምስት በግለሰብ መጋዘን በመራገፍ ላይ እያለ ነው፡፡

የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3- 84 898 ኢት በሆነ የጭነት ተሽከርካሪ የተጫነው የምግብ ዘይት ለቦረናና ባሌ ዞን  ለሚገኙ የድርቅ ተጎጂዎች  መጓጓዝ የነበረበት ቢሆንም  በህገ ወጥ መንገድ በግለሰብ መጋዘን ሲራገፍ ህብረተሰቡ ለፖሊስ ባደረሰው ጥቆማ ሊያዝ ችሏል።

አሽከርካሪው  ለጊዜው ቢሰወረም ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ በክትትል ላይ መሆኑን ጠቁመው የተያዘውን  የምግብ ዘይት ለሚመለከተው አካል ለማስረከብ መዘጋጀቱንም ጠቅሰዋል፡፡

ህብረተሰቡ ህገ ወጥነትን ለመከላከል እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል  ኮማንደር ዲኖ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

 

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ