አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የማስፋፊያ ግንባታ እያካሔደ ነው

21 Apr 2017
274 times

ነቀምቴ ሚያዝያ 13/2009 የወለጋ ዩኒቨርሲቲ  የቅበላ አቅሙን ለማሳደግ  ከግማሽ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ  የማስፋፊያ ግንባታ እያካሄደ መሆኑን ገለፀ ።

የማስፋፊያ ግንባታው ዩኒቨርሲቲው የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥና ለመማር ማስተማር ስራ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ጭምር እንደሚያግዘው   ተመልክተል፡፡ 

በዩኒቨርስቲው የመሰረተ ልማትና የህንፃ ግንባታ ዳይሬክተር ዶክተር ደረጀ አደባ  ለኢዜአ  እንደገለጹት በተለያዩ ጊዜያት የተጀመረው የማስፋፊያ ግንባታው  በ563 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚካሄድ ነው።

በዩኒቨርስቲው  ዋና ግቢን እንዲሁም  በግምቢና በሻምቡ ካምፓሶች እየተካሄደ ካለ የማስፋፊያ ግንባታ  መካከል  የእንስሳት ክሊኒኮች፣የተማሪዎች መዝናኛና መመገቢያ፣ የተማሪዎች መኝታ ክፍሎች ይገኙበታል፡፡

የአስተዳደር ቢሮዎችና የስብሰባ አዳራሾች ፣ የመማሪያና ሌሎች ክፍሎች ጨምሮ አጠቃላይ  ግንባታው  51 ህንፃዎች  የሚያካትት መሆኑን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

የማስፋፊያ ግንባታው በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው   ሁከት መጠነኛ መጓተት ቢያጋጥመውም አሁን ላይ  ስራው 82 በመቶ  መድረሱንና  በሚቀጥለው ዓመት ለአገልግሎት  እንደሚበቃ ይጠበቃል፡፡

ስራው ሙሉ በመሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ሲበቃም የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች  የቅበላ አቅሙን  ከ12 ሺህ ወደ 17 ሺህ ከፍ እንደሚያደርገው ዶክተር ደረጀ ጠቁመዋል፡፡

የማስፋፊያው ግንባታ ለ8 ሺህ የአካባቢው ሰዎች ጊዜያዊ  የስራ ዕድል ፈጥሯል ።

የስራ እድል ከተፈጠረላቸው መካከል   ወጣት ታምራት ሃይሉ በሰጠው አስተያየት ከነቀምቴ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ  በመንገድ ግንባታ ሙያ  ተመርቆ  ስራ አጥቶ መቆጠየቱን ተናግሯል፡፡

ወጣቱ እንዳለው ዩኒቨርሲቲው በጀመረው የግንባታ ፕሮጀክት ውስጥ ተቀጥሮ  በመስራት ራሱንና ቤተሰቡን እየረዳ ነው፡፡

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ