አርዕስተ ዜና

ቢሮው ከ14 ሺህ በላይ ስራ ፈላጊዎችን ከአሰሪ ተቋማት ጋር አገናኝቷል

17 Feb 2017
321 times

አዲስ አበባ የካቲት 10/2009 ከአሰሪ ተቋማት ጋር ግንኙነት በመፍጠር 14 ሺህ 337 ዜጎች ስራ እንዲያገኙ ማድረጉን የአዲስ አበባ ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለጸ።

በቢሮው የአሰሪና ሰራተኛ ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ አበባ እሸቴ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ወጣቶችን የስራ ባለቤት ለማድረግ ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ የቤት ለቤት ምዝገባ ተካሂዷል።

በ2009 በጀት ዓመት አጋማሽ ከ80 ሺህ በላይ ስራ ፈላጊዎች መመዝገባቸውንና 70 በመቶ ያህሉም ወጣቶች እንደሆኑ ገልጸዋል።

የተለያየ ሙያ ያላቸውን እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ተመራቂዎችን ከአሰሪ ተቋማትና ኤጀንሲዎች ጋር በመነጋገር ስራ ማስያዝ እንደተቻለም ተናግረዋል።

የስራ ስምሪቱ የቀጣሪ ድርጅቶችና የስራ ፈላጊዎችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ እንደሆነም ነው ያስረዱት።

በበጀት ዓመቱ የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት በቀጣይ ከአገር ውስጥ የስራ ዕድሎች በተጨማሪ የውጭ አገር የስራ ስምሪት ተጠቃሚ ለማድረግ ዝግጅት መጀመሩንም ወይዘሮ አበባ ተናግረዋል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ