አርዕስተ ዜና

ኮሌጁ የድህረ ምረቃ ትምህርት ሊጀምር ነው

17 Feb 2017
650 times

አዲስ አበባ የካቲት 10/2009 የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ  በአምስት የጤና ህክምና ዘርፎች የድህረ ምረቃ መርሃ ግብር በቀጣዩ ዓመት ሊጀምር መሆኑን ገለፀ።

ኮሌጁ ለአምስት ዓመታት በጠቅላላ ህክምና ትምህርት ዘርፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለጠናቸውን  52 ሀኪሞችን እሁድ ያስመርቃል። ከተመራቂዎቹ መካከል13ቱ ሴቶች ናቸው።

የኮሌጁ ፕሮቮስት ዶክተር ዳንኤል አበበ የምረቃ ሥነ ስርዓቱን አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ  ላይ እንደተናገሩት፤ ሜዲካል ኮሌጁ በመስከረም በአምስት የህክምናው ትምህርት ዘርፎች የድህረ ምረቃ መርሃ ግብር ይጀምራል።

መርሃ ግብሩ  የህጻናት፣ የማህጸንና የውስጥ ደዌ ህክምናዎች፣ የቀዶ ህክምና እንዲሁም የነርሶች ስፔሻሊቲ ትምህርትን ያካተተ መሆኑንም ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ለአምስት ዓመት የጠቅላላ ህክምና ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሐኪሞች ያስመርቃል።

ተመራቂዎቹ ቀደም ብሎ በአዲሱ የከፍተኛ ትምህርት ስርዓት መሰረት በሳይንስ ዘርፍ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸውና የመመዘኛ መስፈርት አልፈው ወደ ኮሌጁ የገቡ ናቸው።

በመርሃ ግብሩ መሰረት ሥልጠና መስጠቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ የባለሙያዎችን ቁጥር ለመጨመር አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ገልጸዋል።

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ከህክምና አገልግሎት ባለፈ የህክምና ሙያተኞችን ማሰልጠን ከጀመረ አምስት ዓመት ሞልቶታል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ