አርዕስተ ዜና

በጎንደር ከተማ አንድ ሆቴል ውስጥ የተወረወረ ቦንብ ጉዳት አደረሰ

11 Jan 2017
813 times

ጎንደር ጥር 3/2009 በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ክልል በሚገኝ አንድ ሆቴል ውስጥ ትናንት ምሽት የተወረወረ የእጅ ቦንብ የአንድ ሰው ህይወት ማጥፋቱንና ሌሎች 11 ሰዎችን  ደግሞ ማቁሰሉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የከተማው ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ዋና ኢንስፔክተር ማረልኝ  ወንድም ዛሬ እንደገለጹት አደጋው የደረሰው በሆቴሉ ይዝናኑ በነበሩ ሰዎች ላይ ምሽት ሁለት ሰዓት አካባቢ ነው፡፡

በአደጋው ህይወቱ ካለፈው ሌላ ሶስት ሰዎች ከባድና ስምንት ሰዎች ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 7 ሰዎች በጎንደር ዩንቨርሲቲ ሆስፒታል ተኝተው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው፤  ቀሪዎቹ በዚሁ ሆስፒታል ታክመው ወደየመኖሪያ አካባቢቸው መሄዳቸውም ተመልክቷል፡፡ 

ፖሊስ አደጋ አድራሾቹን ለመያዝ ክትትል እያደረገ ነው ያሉት ዋና ኢንስፔክተሩ በአደጋው ዙሪያ የሚያገኘው መረጃ  ለህዝብ ይፋ ይደረጋል ብለዋል፡፡ 

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ

<!-Foreign Exchange Rates widget - HTML code - fx-rate.net -->

<!-end of code-->

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ