አርዕስተ ዜና

ለሃላፊነት ክብር ሰጥቶ የሚያገለግል የመንግስት ሰራተኛና አመራር እንዲፈጠር የመንግስት ጽኑ ፍላጎት ነው

315 times

ሚያዝያ 7/2010 በስነምግባር የታነጸ ሙያውን አክብሮ ለሃላፊነት ክብር ሰጥቶ የሚያገለግል የመንግስት ሰራተኛና አመራር እንዲፈጠር የመንግስት ጽኑ ፍላጎት መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሩ"የፍቅርና የአንድነት ኪዳን" በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ በሚሌኒየም አዳራሽ በተካሄደው ውይይት በሃገሪቱ ለተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች  መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

በስነምግባር የታነጸ የአገልግሎት መንፈስ የተላበሰ ሰራተኛ እንዲኖር ጉቦና የጥቅም ሽርክና ዝምድናና አድሏዊ አሰራረር ጎጂ ባህል መሆኑን አውቆ ሙያውን አክብሮ ለሃላፊነት ክብር ሰጥቶ የሚያገለግል የመንግስት ሰራተኛና አመራር እንዲፈጠር ከመንግስት በኩል ጽኑ ፍላጎት እንዳለ አረጋግጠዋል፡፡

ይህን ለማሳካትም በመንግስት መዋቅር ውስጥ የሚደረግ ምደባ በእውቀት በክህሎትና ችሎታ ትክክለኛ ትክክለኛውን ሰው በትክክለኛ ቦታ እንዲሰማራ በማድረግ የመንግስት የማስፈጸም ብቃትን ማሻሻልከሚወሰዱ እርምጃዎች መካከል ተጠቃሽ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ውጤታማ ባልሆነ የተንዛዛ ስብሰባ የሚባክነውን ጊዜና ንብረት በመቀነስ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ለህዝብ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ስርአት ለመዘርጋት ተገቢ ምላሽ የማይሰጥ የመንግስት ሰራተኛም ሆነ ተቋም ተጠያቂ ማድረግ የሚያስችል አካሄድ በመዘርጋት ችግሩን ለመቅረፍ ህዝቡን ባሳተፈ መልኩ እንደሚሰሩ ጠቅላይ ሚንስትሩ አረጋግጠዋል፡፡

በውይይቱ ከ25 ሽህ በላይ ታዳሚዎች ተገኝተዋል፡፡

Last modified on Monday, 16 April 2018 19:12
Rate this item
(0 votes)

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን