አርዕስተ ዜና

ድርጅቶቹ ለጋራ ሀገራዊ ተልዕኮ መሳካት የድርሻቸውን እንዲወጡ ህወሓት ጥሪ አቀረበ Featured

11 Jan 2018
259 times

መቀሌ ጥር 3/2010 የኢህአዴግ እህትና አጋር ድርጅቶች ሀሳባቸውን  በነጻነት በማቅረብ ለጋራ ሀገራዊ ተልዕኮ መሳካት የድርሻቸውን እንዲወጡ ህወሓት ጥሪ አቀረበ።

 ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ባዘጋጀው ሰባተኛ ድርጅታዊ ኮንፍረንስ ላይ ከኢህአደግ አባልና አጋር ድርጅቶች የመጡ ከ200 በላይ ከፍትኛ አመራር አባላት በመሳተፍ ላይ ናቸው ፡፡

 ዛሬ በተጀመረው ሰባተኛ ድርጅታዊ ኮንፍረንስ ላይ የህወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እንዳሉት በኮንፈረንሱ ላይ የኢህአዴግ አባልና አጋር ድርጅቶች ሀሳባቸውን በነጻናት እንዲሰጡ፣ እንዲተቹና እንዲከራከሩ ህወሓት ይፈልጋል፡፡

 በእህትና አጋር ድርጅቶች መካከል ይስተዋል የነበረውን ተቀራርቦ ያለመስራት ክፍተት ለመስበር አንዱ መፍትሄ ህወሓት የሚያዘጋጃቸውን መድረኮች ለድርጅቶቹ ክፍት ማድረግ እንደሆነ ተናግረዋል።

 " ይህም ክልላዊና ሀጋራዊ ተልዕኮን በጋራ ለመወጣት ጠቃሚ እርምጃ መሆኑን ህወሓት ያምናል" ብለዋል፡፡

 በመሆኑም የተለያዩ የኢህአዴግ አባልና አጋር ድርጅቶችን ወክለው በኮንፈረንሱ ላይ የተገኙ ከፍትኛ የአመራር አባላት ሀሳባቸውን በነጻነት አንስተው እንዲከራከሩ  ዶክተር ደብረጽዮን ጥሪ አቅርበዋል፡፡

 ህወሓት ህገ መንግስቱን አክብረው ለጋራ ክልላዊና ሀገራዊ ጥቅም ከሚሰሩ ተቋዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋራ ተቀራርቦ  ለመስራት ዝግጁ መሆኑንም ዶክተር ደብረጽዮን አስታውቀዋል፡፡

 የህወሓት ሰባተኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ለሚቀጥሉት ስምንት ቀናት የህወሓት ማዕካለዊ ኮሚቴ ባካሄደው ግምገማ ያያቸውንና ያልታዩ አዳዲስ ሀሳቦችን አንስቶ ይገመግማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

 

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ