አርዕስተ ዜና

አሜሪካና እንግሊዝ የተኩስ አቁም ስምምነቱን የሚጥሱ የደቡብ ሱዳን ተፋላሚዎችን አስጠነቀቁ

02 Jan 2018
376 times

ታህሳስ 24/2010 አሜሪካ፣ እንግሊዝና ኖርዌይ በደቡብ ሱዳን ግጭት እጃቸውን ያስገቡ  ፓርቲዎችና የጦር አዛዦቻቸው የተኩስ አቁም ስምምነቱን እንዲያከብሩ  ጠየቁ፡፡

ሀገራቱ የተኩስ አቁም ስምምነቱን በሚጥሱ ግለሰቦችም ሆነ ቡድኖች ላይ  ቅጣት እንደሚጥሉም ነው ሮይተርስ የዘገበው፡፡

በሀገሪቱ ለአራት ዓመታት የዘለቀውን የእርስ በእርስ ጦርነት ለማስቆምና  እኤአ የ2015ቱን የሰላም ድርድር መልሶ ለማስቀጠል ይረዳ ዘንድ በቅርቡ ተፋላሚ ወገኖች ኢትዮጵያ ውስጥ የተኩስ አቁም ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡

የተኩስ አቁም ስምምነቱ ሰብዓዊ እርዳታ የሚያደርጉ አካላት በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ሰብዓዊ እርዳታ የሚያደርሱበትን ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል የሚል ተስፋ ተጥሎበትም ነበር፡፡

ሶስቱ ምዕራባውያን ሀገሮች በጋራ ባወጡት መግለጫ  ስምምነቱን የፈረሙ ፓርቲዎችና የጦር መሪዎቻቸው ማነኛውንም ወታደራዊ እርምጃ እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

 የተኩስ አቁም ስምምነቱን የሚጥሱና ሰብኣዊ እርዳታውን የሚያስተጓጉሉ የጦር አዛዦችና የፖለቲካ መሪዎቻቸው ተጠያቂ እንደሚሆኑም በመግለጫቸው አስታውቀዋል፡፡

ዘገባው እስከተጠናቀረበት ድረስ መግለጫውን አስመልክቶ ከተቃዋሚ ሃይሎች  የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡

የተኩስ አቁም ስምምነቱን ተከትሎ ተቀናቃኝ ሃይሎች ስልጣን በሚጋሩበትና አዲስ ምርጫ የሚያካሂዱበትን ቀን ለመቁረጥ የሚያስችሉ ውይቶችን ለማድረግ ታስቦ እንደነበርም ነው የቻይናው ዓለም አቀፍ ቴሌቪዥን ኔትዎርክ የዘገበው፡፡

ኢጋድም የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ሃይሎች በቅርቡ አዲስ አበባ ውስጥ የተፈራረሙት የተኩስ አቁም ስምምነት መጣሱን አውግዟል፡፡

በ28ኛው የኢጋድ የመሪዎች ጉባኤ የተላለፈውን የውሳኔ ሃሳብ መሰረት አድርጎ ምክር ቤቱ ስምምነቱን የጣሱትን ሃይሎች ተጠያቂ እንደሚያደርግ  የኢጋድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊቀ መንበር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ተናግረዋል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ