አርዕስተ ዜና

ኡጋንዳ ጦሯን ከሶማሊያ ማስወጣት ጀመረች

07 Dec 2017
661 times

አዲስ አበባ ህዳር 28/2010 ኡጋንዳ በሶማሊያ ያሰማራቻቸውን ሰላም አስከባሪ ጦር ማስወጣት ጀመረች።

ኡጋንዳ በሶማሊያ የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ጦር (አሚሶም) ጥላ ስር ካሰማራቻቸው ስድስት ሺህ ጦር ውስጥ 281 ወታደሮችን ማስወጣት መጀመሯን ቢቢሲ በዘገባው አስታውቋል፡፡

ቅነሳው የተባበሩት መንግስታት በሶማሊያ ያለው የሰላም አስከባሪ ጦር እኤአ በ 2017 ማብቂያ ድረስ የአሚሶም ጠር በ 1 ሺ እንዲቀንስ የሰጠውን ትዕዛዝ ተከትሎ የሚተገበር መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ሰላም ማስከበር ተልእኮ ስር ከኢትዮጵያ፣ኡጋንዳ፣ቡሩንዲ፣ኬንያ እና ጅቡቲ የተውጣጡ ከ20 ሺህ በላይ ሰላም አስከባሪዎች በሶማሊያ ተሰማርተዋል፡፡

ኬንያ፣ቡሩንዲ፣ጅቡቲና ኢትዮጰያ እስከ ፈረንጆቹ 2017 ማብቂያ ወታደሮቻቸውን እንደሚቀንሱ ይጠበቃል፡፡

አንድ ሺህ ወታደሮችን መቀነስ ፈጣን ውጤት የሚያመጣ ባይሆንም አሚሶምን የሚደግፉ አለም አቀፍ አጋሮች የሶማሊያን ብሔራዊ ጦር የማጠናከሩ ስራ መሰረት እየያዘ በመምጣቱ ሰላም አስከባሪ ሀይሎችን መቀነስ እንዳለበት ታምኖበታል፡፡

የአፍሪካ ሰላም አስከባሪዎች በአገሪቱ የፈጠሩት መረጋጋት አድናቆት የሚቸረው ቢሆንም አልፎ አልፎ አልሻባብ በአገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች በንጹሃን ዜጎች ላይ ጥቃት እንዳይፈጽም ማድረግ አለመቻሉ ተገልጿል፡፡

አሜሪካ ከሶማሊያ ጦር ሰራዊት ጋር ያላትን ትብብር በማሳደግ በአገሪቱ ያላትን ጦር ወደ 500 በማሳደግ በሽብር ቡድኑ ላይ የአየር ላይ ጥቃት በመፈጸም ላይ ትገኛለች፡፡

በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ከሁለት ወር በፊት በደረሰ የቦምብ ጥቃት 500 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን በተባበሩት መንግስታት በሚደገፉ አገራት ከደረሰው አደጋ የላቀው መሆኑን ዘገባው አስታውሷል፡፡

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ