አርዕስተ ዜና

10ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን የተጀመረው የልማትና የሕዳሴ ጉዞን በሚያጠናክር መልኩ ይከበራል Featured

12 Oct 2017
475 times

ጋምቤላ ጥቅምት 2/2010  አስረኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በክልል ደረጃ የተጀመረውን የልማትና የሕዳሴ ጉዞ በሚያጠናክር መልኩ ለማክበር ዝግጅት መደረጉን የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት አስታወቁ።

 በዓሉ ''ራዕይ ሰንቀናል፤ ለላቀ ድል ተነስተናል" በሚል መሪ ቃል በክልሉ እንደሚከበርም ተገልጿል።

 የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤው አቶ ጁል ናንጋል በዓሉን አስመልከተው ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት በዓሉን የተጀመሩ የልማት፣ የፀረ- ድህነትና የህዳሴ ጉዞ መስመሮችን በሚያጠናክር መልኩ ከጥቅምት 6 ቀን 2010 ዓም ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች በክልል ደረጃ ለማክበር ዝግጅት ተደርጓል።

 የሰንደቅ ዓላማ ቀን ባለፉት ዓመታት የተገኙ የልማት ስኬቶችና የተጀመረውን የህዳሴ ጉዞ ለማስቀጠል ሕብረተሰቡ በድጋሚ ቃሉን የሚያድስበት ዕለት መሆኑንም ተናግረዋል።

 የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ አንድነታቸውን በማጎልበት በድህነት ላይ በጋራ የጀመሩትን ዘመቻ የሚያጠናክሩበት ቀን እንደሚሆንም  አቶ ጁል አያይዘው ገልጸዋል።

 በዓሉ በክልሉ የህዝቦችን አብሮነትና አንድነት በሚያጠናክርና የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን ቀጣይነት በሚያረጋግጥ መልኩ እንደሚከበርም ብለዋል።

 እንደምክትል አፈጉባኤው ገለጻ በአሁኑ ወቅት የሰንደቅ ዓላማ ቀንን በክልሉ ሁሉም ዞኖች፣ ወረዳዎችና ትምህርት ቤቶች በፓናል ውይይት፣በሰልፍ ትርኢት፣ ሰንደቅ ዓላማ በመስቀልና በተለያዩ ዝግጅቶች ለማክበር በየደረጃው የበዓል አዘጋጅ ኮሚቴዎች ተቋቁሞ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኙ ተናገረዋል፡፡

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ