አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

ኮሚሽኑ ቻድ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ረገድ እያደረገች ያለውን እንቅስቃሴ አደነቀ Featured

12 Sep 2017
331 times

አዲስ አበባ መስከረም 2/2010 ሰሜን አፍሪካዊቷ አገር ቻድ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ረገድ እያደረገች ያለው እንቅስቃሴ የሚደነቅ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ገለጸ።

የኮሚሽኑ ዋና ፀሀፊ ሚስ ቬራ ሶንግዌ ከቻድ ፕሬዚዳንት እድሪስ ዴቤ ጋር ባለፈው ሐሙስ በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ መክረዋል።    

ለሁለት ቀናት የተካሄደው ይሄው ምክክር የቻድን ብሄራዊ ልማት እቅድ በገንዘብ መደገፍ በሚቻልበት ዙሪያ ላይ ያተኮረ ነበር። 

ዋና ፀሀፊ ቬራ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ቻድ በቀጣናው ሠላምና መረጋጋት እንዲሰፍን እየተጫወተች ያለው ሚና የሚደነቅ ነው።

በተለይ አሸባሪው ቡድን ቦኮሀራም ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት በመሰንዘር ትልቅ አህጉራዊ ኃላፊነቷን እየተወጣች መሆኑን ነው የጠቀሱት።

''ዘላቂነት ያለው ልማት ለማምጣት ሰላምና መረጋጋትን ማረጋገጥ ወሳኝ'' ነው ያሉት ኮሚሽነር ቬራ ቻድ ፤ በዚህ ረገድ ለምታደርገው አስተዋጽኦ እውቅና እንደሚሰጥ ተናግራዋል። 

ቻድ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2017 እስከ 2021 ለመተግበር ያወጣችው ብሄራዊ የልማት እቅድ ውጤታማ እንዲሆን ኮሚሽኑ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

 

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ