አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

ሶማሊያ ፌደራላዊ ስርዓቷን ለማጎልበት ከኢትዮጵያ የተሻለ ልምድ አግኝታለች…. የሶማሊያ መንግሥት ልዑክ Featured

13 Aug 2017
564 times

አዲስ አበባ ነሐሴ 6/2009 ሶማሊያ ፌደራላዊ ስረዓቷን ለማጎልበት የኢትዮጵያ  ፌደራላዊ  አወቃቀር  የተሻለ ሆኖ እንዳገኘው  ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የሚገኘው የሶማሊያ መንግሥት ልዑክ ገለጸ።

ልዑኩ በአምስት ቀናት የኢትዮጵያ ቆይታው በትግራይና አማራ ክልሎች ባደረገው ጉብኝትም  የፌደራሊዝም አወቃቀሩን አስመልክቶ በርካታ ተሞክሮዎችን ማግኘቱን ነው የገለጸው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ልዑኩ ጉዳዩን አስመልክተው በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

ልዑኩን የመሩት የሶማሊያ የአገር ውስጥና የፌዴራል ዕርቀ ሠላም ሚኒስቴር ቋሚ ፀሐፊ  አብዱላሂ መሐሙድ ሐሰን እንደገለጹት ሶማሊያ በጎሳ ግጭትና  በአሸባሪዎች ስትታመስ ቆይታለች።

በሶማሊያ ሽብርተኝነትን  ለመዋጋትና ዘላቂ ሠላምን ለማሰፈን  የፌዴራል ሥርዓት መዘርጋት  አስፈላጊ መሆኑን የገለጹት ቋሚ ጸሀፊው  መንግሥታቸው ሥርዓቱን ለማጠናከር በርካታ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ አብራርተዋል።  

የሀገሪቱን የፌደራል ሥርዓት ለማጎልበት በኬንያና በስዊዘርላንድ ተመሳሳይ የልምድ ልውውጥ መደረጉን የተናገሩት የልዑኩ መሪ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ሥርዓት ከአገራቸው ባህልና ነባራዊ ሁኔታ አንፃር የተሻለ መሆኑን ጠቁመዋል።  

ልዑኩ ለልምድ ተሞክሮ በተንቀሳቀሰባቸው ክልሎችና በፌደራሉ መንግስት የተደረገለትን አቀባበልም አድንቋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ በበኩላቸው  ሁለቱ ሀገራት  በተለይ በሠላምና ፀጥታ፣ በመሰረተ ልማት፣  በምጣኔ ኃብታዊና ማህበራዊ  ጉዳዮች ግንኙነቶቻቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

ልዑኩ ወደ ሶማሊያ ሲመለስም  ያገኘውን ተሞክሮ በመቀመር የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የማሸጋገር ሚናውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ 

ለሁለቱ ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት ኢትዮጵያ በቁርጠኝነት እንደምትሰራም ነው ሚንስትር ዴዔታዋ ያረጋገጡት

የሶማሊያ መንግሥት ልዑክ ከኢትዮጵያ የፌዴራል ሥርዓት፣ ገቢ አሰባሰብ፣ ከተማ ልማትና ግጭት አፈታት ስርዓቷ እንዲሁም  ከፌደሬሽን ምክር ቤት አወቃቀርና ተያያዥ ጉዳዮች  ልምድ ለመውሰድ ነው በኢትዮጵያ ቆይታ ያደረገው።

 

 

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ