አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

ህብረተሰቡ ሙሰኞችን የማጋለጡን ስራ እንዲቀጥልበት ጥሪ ቀረበ Featured

12 Aug 2017
461 times

አዲስ አበባ  ነሃሴ 5/2009 የመንግሥትና የህዝብን ሃብት በመመዝበር የተጠረጠሩ ባለስልጣናት እና ግለሰቦችን በማጋለጥ በኩል ህብረተሰቡ እያደገረ ያለውን ጥረት እንዲቀጥል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አሳሰበ።

 የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት በሳምንታዊ አቋም መግለጫው እንዳለው የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊና ሌሎች ችግሮችን ለመፍታት መንግስት በየዓመቱ ከፍተኛ በጀት ይመድባል።

 ይሁንና ይህንን የህዝብና የመንግስት ሃብት ከህግ ውጭ ላልታለመለት ዓላማ ሲያውሉ የነበሩ አስፈጻሚዎችንና ሌሎች ተዋናዮችን በህግ የመጠየቁ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ጽህፈት ቤቱ በመግለጫው አስታውቋል ።

 በኢፌዴሪ ህገ መንግሥት፣ የመንግስት አሰራር ለሕዝብ ግልፅ መሆን እንዳለበት፣ ማንኛውም የመንግስት ባለስልጣን ወይም የህዝብ ተመራጭ ጥፋት ፈጽሞ ሲገኝ ከሃላፊነቱ እንደሚነሳና ተጠያቂ እንደሚሆን ተደንግጓል።

 በተወካዩ ላይ አመኔታ ሲያጣም በማንኛውም ጊዜ ሊያነሳው ህዝብ መብት ተሰጥቶታል፡፡

 ሰሞኑን በተከታታይ እንደታየው የመንግሥትንና የህዝብን ሃብትና ንብረት  በመመዝበር የተጠረጠሩ ባለስልጣናትና ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር የሚውሉበትና ለህግ የሚቀርቡበት ሁኔታ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በአንዳንድ አካባቢዎች የተደራጁ ወንጀለኞችንም በቁጥጥር ሥር የማዋል እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል።

የኪራይ ሰብሳቢነትን አመለካከትና ተግባር ከምንጩ ማድረቅ የምንችለው በአቋራጭ መበልፀግን የሚፀየፍ እና በምትኩም ልማታዊ አስተሳሰብን በተሟላ አኳኋን የሚቀበል ህብረተሰብ መፍጠር ሲቻል ነው።

ይሁንና የፀረ ኪራይ ሰብሳቢነት ትግሉ የታለመለትን ዓላማ ማሳካት የሚችለው ከመንግሥት አካላት ውጭ ያሉ በርካታ ተዋናዮች ራሳቸውን ለትግሉ ማሰለፍ ሲችሉ እንደሆነም መንግሥት ያምናል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ በመልካም አስተዳደር ችግሮችና በኪራይ ሰብሳቢነት እጃቸው አለበት ያላቸውን የመንግሥት ባለሥልጣናትና ሌሎች አካላትን በማጋለጥና ከጸጥታና የፍትህ አካላት ጋር በመተባበር የተጫወተውን ሚና አጠናክሮ እንዲቀጥል ጽህፈት ቤቱ አሳስቧል

 የጽህፈት ቤቱ ሙሉ የአቋም መግለጫም እንደሚከተለው ቀርቧል።

 በኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የተዘጋጀ

ሳምንታዊ አቋም መግለጫ

ነሃሴ 5  ቀን 2009 ዓ.ም

በአመለካከት ለውጥ የታገዘ የጸረ ኪራይ ሰብሳቢነት ትግል እናፋጥን!

በኢፌዴሪ ህገ መንግሥት፣ የመንግስት አሰራር ለሕዝብ ግልፅ መሆን እንዳለበት፣ ማንኛውም የመንግስት ባለስልጣን ወይም የህዝብ ተመራጭ ጥፋት ፈጽሞ ሲገኝ ከሃላፊነቱ እንደሚነሳና ተጠያቂ እንደሚሆን ተደንግጓል። በተወካዩ ላይ አመኔታ ሲያጣም በማንኛውም ጊዜ ሊያነሳው ህዝብ መብት ተሰጥቶታል፡፡ በአጠቃላይ ስልጣን የሚመነጨውም ሆነ ጥቅም ላይ የሚውለው ከህዝብና ለህዝብ መሆኑን ያረጋገጠ፣ ማንኛውም ባለስልጣን ከህዝብ በታች መሆኑንና ጥፋት መፈጸሙ በማስረጃ ሲረጋገጥበትም ከህግ ተጠያቂነት እንደማያመልጥ በህገ መንግሥቱና በሌሎች ህጎችም በግልጽ ተሰምሮበት ያደረ ጉዳይ ነው።

ሰሞኑን በተከታታይ እንደታየው የመንግሥትን እና የህዝብን ሃብትና ንብረት ያላግባባብ በመመዝበር የተጠረጠሩ ባለስልጣናት እና ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር የሚውሉበትና ለህግ የሚቀርቡበት ሁኔታ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ወደፊትም ይኸው ሁኔታ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። በእስካሁኑ ሂደት እንደታየው ከተጠርጣሪዎች ጋር በመመሳጠር በዘረፋ የተጠረጠሩ ባለሃብቶችም ይሁኑ የንግድ ኩባንያዎች ከህግ ተጠያቂነት እንደማያመልጡ በተግባር እየተረጋገጠ መጥቷል። በአንዳንድ አካባቢዎች የተደራጁ ወንጀለኞችንም በቁጥጥር ሥር የማዋል እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል።

ስልጣንን አላግባብ በመጠቀም በመንግስትና በህዝብ ኃብት ላይ ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉና ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እንዲታይ መደረጉ በአገራችን የሕግ የበላይነት የተረጋገጠበት ስርዓት በአስተማማኝ ሁኔታ ለመገንባቱ ዓይነተኛ ማሳያ ነው። በሌላ በኩል ተፈጽመዋል የተባሉ የሙስና ተግባራትን በዝርዝር በማጥናት እና በማጣራት ረዘም ያለ ሂደት እንዲያልፉ መደረጉም የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዳይሸራረፉ የተደረገውን ጥንቃቄ አመላካች ነው።

ከሁሉ በላይ ደግሞ የጸረ ኪራይ ሰብሳቢነት ትግሉ የሚሰምረው በተደራጀ የህዝብ ተሳትፎ ሲመራ ብቻ ነው የሚለው የመንግሥት አቋም ህዝባዊነቱን ዳግም ያረጋገጠበት ሌላው ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይገባል። የኪራይ ሰብሳቢነትን አመለካከትና ተግባር ከምንጩ ማድረቅ የምንችለው በአቋራጭ መበልፀግን የሚፀየፍ እና በምትኩም ልማታዊ አስተሳሰብን በተሟላ አኳሃን የሚቀበል ህብረተሰብ መፍጠር ስንችል ነው። ይህ ሲሆን ነው ለዘላቂ ድል የምንበቃው።  የጸረ ኪራይ ሰብሳቢነት ትግሉ የአንድ ወቅት ስራ አይደለም የሚባለውም በዚሁ ምክንያት መሆኑ ሊታወቅ ይገባዋል። ጉዳዩ የተዛባ አመለካከትን የመለወጥ እና ልማታዊ አስተሳሰብን የመገንባት ሂደት እንደመሆኑ ረዘም ያለ ጊዜ የሚወስድ መሆኑ አያጠያይቅም። ይህም ሥርዓታችን በባህርይው ኪራይ ሰብሳቢነትን ከምንጩ ለማድረቅ የተሟላ ቁርጠኝነት እንዳለው ተጨባጭ ማሳያ ነው። በማንኛውም ጊዜ ስህተቶቹን ፈጥኖ የሚቀበልና ራሱን በራሱ የሚያርም መሆኑም ሌላው የሥርዓቱ መገለጫ ባህርይ ነው።

ይሁንና የፀረ ኪራይ ሰብሳቢነት ትግሉ የታለመለትን ዓላማ ማሳካት የሚችለው ከመንግሥት አካላት ውጭ ያሉ በርካታ ተዋናዮች ራሳቸውን ለትግሉ ማሰለፍ ሲችሉ እንደሆነም መንግሥት ያምናል። ከዚህ አንጻር በተለይ የአገራችን ሚዲያዎች ከሥራ ባህርያቸውና ከተጣለባቸው ሃላፊነት አንጻር የህዝብን አመለካከት በመለወጥ እና የኪራይ ሰብሳቢነት ተግባራትን በተጨባጭ ማስረጃዎች አስደግፈው በማጋለጥ ረገድ ገንቢ ሚና መጫዎት ይጠበቅባቸዋል።

ከሁሉ በላይ ደግሞ የፀረ ኪራይ ሰብሳቢነት ትግሉን እየመራ ያለው ህዝባችን ይህንኑ ትግል አጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል። በመልካም አስተዳደር ችግር እና በኪራይ ሰብሳቢነት እጃቸው አለበት ያላቸውን የመንግሥት ባለሥልጣናትና ሌሎች አካላት በህዝባዊ መድረኮች ላይ ፊት ለፊት በማጋለጥ እና ከጸጥታና የፍትህ አካላት ጋር በመተባበር ረገድ የተጫወተውን ዓይነተኛ ሚና አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል። ከእንግዲህ አገራችን ለኪራይ ሰብሳቢዎች ፍጹም እንደማትመችም በተግባር ሊያረጋግጥላቸው የሚችለው በዋነኝነት በህዝቡ ግንባር ቀደም ተዋናይነት እንደሆነ በውል ተረድቶት ከፊት ረድፍ ሆኖ እያካሄደው ያለውን ትግል ይበልጥ አፋፍሞ መቀጠል ይኖርበታል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ