አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

በባህርዳር ከተማ ዛሬ በከፊል አገልግሎት መስጠት ያቆሙ ሱቆችና ተሽከርካሪዎች ወደ ስራ ገቡ Featured

07 Aug 2017
663 times

ባህርዳር  ነሀሴ 1/2009  በባህርዳር ከተማ በህገ-ወጥ መንገድ አገልግሎት መስጠት ለማቆም የሞከሩ የንግድ ተቋማትና ተሽከርካሪዎች ወደ ስራ እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑን የከተማው አስተዳደር ገለጸ።

 በከተማዋ በመንገድ ላይ ትላንት ምሽት የተጣለው ቦምብ በሰውም ሆነ በንብረት ላይ ጉዳት አለማድረሱን የከተማው ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

 የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አየነው በላይ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት በህገ-ወጥ መንገድ በከፊል ስራ ያቆሙ የንግድ ሱቆችና ተሽከርካሪዎች ወደ ስራ እየገቡ ይገኛሉ።

 በዚህም አመራሩ የንግዱን ማህበረሰብ በማነጋገር የተዘጉ ሱቆች እንዲከፈቱ እያደረገ ሲሆን ዛሬ ጠዋት ላይ በከፊል አገልግሎት መስጠት አቁመው የነበሩ ተሽከርካሪዎችም ወደ ስራ እንዲገቡ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

 የአስተዳደሩ ንግድ፤ ኢንዱስትሪና ገበያ ልማት መምሪያ ተወካይ ወይዘሮ እመቤት አሰፋ በበኩላቸው የተዘጉ ሱቆችን ከማሸግ ይልቅ የንግዱን ማህበረሰብ ቤት ለቤት በመዘዋወርና በማነጋገር እንዲከፍቱ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

 የከተማው ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ዋለልኝ ዳኛው እንደገለጹት ትላንት ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ከ25 አካባቢ ከፖሊ ወደ ፔዳ በሚወስደው የአስፓልት መንገድ ላይ የተጣለው አንድ ቦምብ በሰውም ሆነ በንብረት ላይ ጉዳት አላደረሰም።

 ከወንጀሉ ጋር በተያያዘ አምስት ተጠርጣሪዎችና ለዚሁ ጉዳይ የዋለ ሚኒባስ ተሽከርካሪም በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

 በህገ-ወጥ መንገድ በማህበራዊ ሚዲያ የተጠራው የስራ ማቆም አድማም የተረጋገጠውን ሰላም የሽብር ኃይሎች ሆን ብለው ለማደፍረስ ያቀዱት ሴራ መሆኑን ጠቁመዋል።

 መምሪያውም የፀጥታ ኃይሉን ቀድሞ በማሰማራት የከተማዋ ፀጥታና የህዝቡ ሰላም እንዲረጋገጥ ነቅቶ እየሰራ እንደሚገኝም አስታውቀዋል። 

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ