አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ Featured

17 Jul 2017
1401 times

አዲስ አበባ ሐምሌ 10/2009 የኢትዮጵያ ማህበረ ዴሞክራሲና ደቡብ ህብረት አንድነት ፓርቲ ስያሜውን ወደ ኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራሲ ፓርቲ  መቀየሩን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ማህበረ ዴሞክራሲ ፓርቲና ደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ሕብረት ውህደት በኋላ ፓርቲው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በታዛቢነት በተገኘበት የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤውን ትናንት አካሂዷል።

በጉባኤውም ፓርቲው ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን  በሊቀ መንበርነት፣ አቶ ጥላሁን እንዳሻውን በምክትል ሊቀመንበርነት፣አምሳ አለቃ በቀለ ጌዴቦን የኦዲትና ኢንስፔክሽን ሃላፊ በማድረግ መርጧል።

በተጨሪም 31 የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴና አምስት ተለዋጭ አባላት ምርጫን ሲያካሂድ  ከ31 ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቱ ውስጥ  11ዱን በስራ አስፈፃሚነት መርጧል።

የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ የፓርቲውን ርዕዮተ ዓለም ለማሳደግ፣ የመጠሪያ ስሙን ለማቅለል፣ በደቡብ ተወላጆች ብቻ የታጠረውን የፓርቲውን ተደራሽነት በክልሉና ከክልሉ ውጭ ለማድረግ የስም ለውጥ ማስፈለጉን ተናግረል።

ኢሶዴፓ ከካፒታሊዝምና ሶሻሊዝም ርዕዮተ ዓለማት የወሰዳቸው ለኢትዮጵያ ህዝብ መልካም ናቸው የሚላቸውን ጠንካራ ጎኖች የያዘ ሶሻል  ዴሞክራሲ እንደሚከተልም ተናግረዋል።

የፓርቲው አመራርና አባላት ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ትግል በማድረግ ለኢትዮጵያ ህዝብ ተጠቃሚነትና መብት መረጋገጥ እንደሚሰሩም ሊቀ መንበሩ በጉባኤው ለተሰብሳቢዎች ቃል ገብተዋል።

ፓርቲው ኢትዮጵያን እርስ በእርስ ለማተረማመስና ዲሞክራሲያዊ ባልሆነ መንገድ ስልጣን ለመያዝ ከሚፈልጉ ፅንፈኛ ሃይሎች ጋር እንደማይሰራም ፕሮፌሰር በየነ አስታውቀዋል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ