አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

ፓርቲዎቹ ተጨማሪ አራት የመደራደሪያ አጀንዳዎችን አጸደቁ Featured

19 Jun 2017
699 times

አዲስ አበባ ሰኔ 12/2009 አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ጋር ለመደራደሪያነት ካቀረቧቸው 13 ርዕሰ ጉዳዮች መካከል አራቱን ዛሬ አጸደቁ፡፡

ሰኔ 7 ቀን 2009 ዓ.ም  ባካሄዱት ውይይት የምርጫ አዋጁን በተመለከተ ለመደራደር የተስማሙ ሲሆን፤ በአጠቃላይ በጋራ ያጸደቋቸው የመደራደሪያ አጀንዳዎች ወደ አምስት ደርሰዋል፡፡

የተለያዩ አዋጆችና ህጎች፣ ብሔራዊ መግባባት፣ የዴሞክራሲዊና ሰብዓዊ ተቋማት አደረጃጀት እንዲሁም ዜጎች በየትኛውም ክልል ተዘዋውረው የመስራት፣ ንብረት የማፍራትና የመደራጀት መብትን በሚመለከት የተቀመጡ የመደራደሪያ አጀንዳዎችን ፖለቲካ ፓርቲዎቹ ዛሬ አጽድቀዋል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በሚመለከት ባነሱት ሀሳብ ተፎካካሪ ፓርቲዎቹ የአገሪቷን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የሚያዳክም እንደሆነ ገልጸዋል።

ኢህአዴግ በበኩሉ፤ አገሪቷ በአስቸኳይ አዋጅ ውስጥ ሆና ስለአዋጁ መወያየት አግባብ እንዳልሆነ ገልጾ፤ አዋጁ ግን በምንም አግባብ የአገሪቷ ኢኮኖሚ ላይ ተጽዕኖ እንዳላመጣ ጠቁሟል፡፡

ሌላው ሰፊ ክርክር የወሰደው “የፓለቲካ እሰረኞች አሉ ወይስ የሉም” የሚለው ሀሳብ ሲሆን፤ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጉዳዩ የድርድር አጀንዳ እንዲሆን ጠይቀዋል።

ኢህአዴግ በበኩሉ፤ በአገሪቷ ውስጥ የፖለቲካ እሰረኛ እንደሌለ ገልጾ፤ በፖለቲካ ውስጥ የነበሩ ቢሆንም የታሰሩት ህግን የተላለፉ መሆናቸውን አስረድቷል።

''ይህ ደግሞ የዴሞክራሲ አንዱ መገለጫ የሆነው የህግ የበላይነት በአገሪቷ ውስጥ እንደሰፈነ ማሳያ ነው'' ብሏል።

የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በተከራከሩባቸውና ኢህአዴግ ባልተቀበላቸው የመደራደሪያ አጀንዳዎች ላይ ድጋሚ ተወያይቶ ለመተማመን ለሰኔ 17 ቀን 2009 ዓ.ም ቀጠሮ ተይዟል።

በአገሪቷ ውስጥ በህጋዊነት የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ጋር ለመደራደር እንቅስቃሴ ከጀመሩበት ቀን አንስቶ  ከአስር ጊዜ በላይ ውይይት አካሄደዋል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ