አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

ፌደራሊዝም የስልጣንን ባለቤትነት ለህዝብ ያሸገገረ ስርዓት ነው--- የአርሲ ዩኒቨርስቲ ምሁራን

19 Jun 2017
1055 times

አዳማ ሰኔ 12/2009 ፌደራሊዝም ዴሞክራሲያዊ የህዝብ ስልጣን ባለቤትነትን ያረጋገጠ ስርዓት መሆኑን በአርሲ ዩኒቨርስቲ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ ምሁራን ገለጹ፡፡

የዩኒቨርስቲው የስነ ዜጋና ስነ ምግባር መምህር አቶ ስሜ የኋላሸት እንደገለጹት  የፌደራል ሥርዓቱ የሀገሪቱ ህዝቦች የጋራ በሆኑት ጉዳዮች ላይ በመተማመንና በመግባባት በልማቱ እኩል እንዲሳተፉ ዕድል የሰጠ ነው።

"ከ40 በመቶ በላይ የዓለም ሀገራትና ህዝቦች በፌደራሊዝም ስርዓት ይተዳደራሉ"  ያሉት አቶ ስሜ የኢትዮጵያን ለየት የሚያደርገው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች አሰፋፈር፣ባህልና ቋንቋን መሰረት በማድረግ እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነትን በማረጋገጡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የፌደራል ሥርዓቱ በክልሎች መካከል ጤናማና በመተማመን ላይ የተመሰረተ መልካም ጉርብትናና የጋራ ልማት እንዲኖር በማድረግ የሀገሪቱን  ታሪክ መቀየሩንም  ጠቅሰዋል፡፡

"የሃይማኖት ነፃነት፣የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ያለገደብ የተከበረባት ሀገር ለመገንባት የፌደራልዝም ሥርዓቱ መሰረት ነው "ያሉት ደግሞ በዩኒቨርሲቲው የተቋማዊ ለውጥ ምክትል ዲን አቶ ሙስበሃ አማን ናቸው።

ህዝቦች የራሳቸውን ዕድል በራስ የመወሰን እስከ መገንጠል ህገ መንግስታዊ መብትና ዋስትና ያገኙበት፣አካባቢያቸውን እንዲያስተዳድሩና እንዲያለሙ፣ባህልና ቋንቋቸውን እንዲያሳድጉ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል፡፡

ምሁሩ እንዳመለከቱት የአሁኑ ትውልድ በሥርዓቱ የተገኙ ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ውጤቶችን የራሱን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ሊያረጋግጥ በሚችል መልኩ ማስቀጠል አለበት።

በዩኒቨርሲቲው ጠቅላላ አገልግሎት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ አሳልፍ ኮኮብ በበኩላቸው ስርዓቱ ዜጎች በራሳቸው መብትና ጥቅም ላይ በጋራ ሆነው በእኩልነት የመወሰን ስልጣን እንዲያገኙ ያስቸለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ 

ሞጋችና መብት ጠያቂ ህብረተሰብ መፈጠሩ የሥርዓቱ ውጤት ቢሆንም በመልካም አስተዳድር ማስፈን፣በፍትህና የህግ የበላይነት ማረጋገጥ ላይ አሁንም በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ሥርዓቱ  አርሶና አርብቶ አደሩን ጨምሮ የሌሎችንም ዜጎች የኑሮ ሁኔታ እንዲለውጥ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን የገለጹት ደግሞ በዩኒቨርሲው የአስተዳደርና የልማት ዘርፍ ምክትል ፕሬዘዳንት ዶክተር ገዘኸኝ ጉርሙ ናቸው፡፡ 

"በማህበራዊ አገልግሎት በተለይም የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ፣የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማስፋፋት፣የቴሎኮም አገልግሎት ተደራሽነት፣የጤና፣የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና የመንገድ ልማት የፌደራል ሥርዓቱ ውጤቶች ናቸው" ብለዋል።

ፌደራሊዝም የነበረውን አሃዳዊ የፖለቲካ መደብ ወደ ዴሞክራሲያዊ የህዝብ ስልጣን ባለቤትነት በማሸጋገር ዜጎች በሁሉም መስክ እኩል ተሳታፊና  ተጠቃሚ እንዲሆኑ ምቹ መደላድል መፍጠሩን   ምሁራኑ ገልጸዋል፡፡

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ