አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

ኢትዮጵያ በኳታርና በባህረ ሰላጤው ሰላም እንዲሰፍን የበኩሏን ትወጣለች Featured

19 Jun 2017
736 times

አዲስ አበባ ሰኔ 12/2009 ኢትዮጵያ በኳታርና በባህረ ሰላጤው አገሮች መካከል ሰላም እንዲሰፍን የበኩሏን እንደምትወጣ አረጋገጠች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የተላከውን መልዕክት ለኩዌት አሚር ሼክ ሳባህ አል አህመድ አል ጃበር አል ሳባህ አቅርበዋል።  በአገሮቹ የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይም ተወያይተዋል።

ዶክተር ወርቅነህ ከአሚሩ ጋር በተወያዩበት ወቅት እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በኳታር እና በባህረ ሰላጤው አገሮች መካከል የተከሰተው ውዝግብ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲፈታ ጽኑ ፍላጎት አላት።

ኩዌት ሁለቱን ወገኖች ለማደራደር የምታደርገውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ኢትዮጵያ እንደምትደግፍ ጠቁመው፤ ጥረቱ ስኬታማ እንዲሆን የበኩሏን አስተዋጽኦ ለማድረግ  ፍላጐቱ እንዳላት አብራርተዋል።

የኩዌቱ አሚር ሼክ ሳባህ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ የዓረቡ ዓለም በተለይም የኩዌት ወዳጅ መሆኗን አስታውሰው፤ አሁንም ችግሩ በውይይት እንዲፈታ ከአፍሪካ ቀዳሚ አገር በመሆን ለምታደርገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በባህረ ሰላጤው የተከሰተው ሁኔታ ከአካባቢው አልፎ በሌሎች አካባቢዎችም ተጽዕኖ እንደሚኖረው አመልክተው፤ ሁሉም አገሮች ድምፃቸውን እንዲያሰሙ ጥሪ አቅርበዋል።

ለሰላማዊ መፍትሄው እውን መሆን ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሠላም እና መረጋጋት እንዲኖር ለምታደርገው ጥረት አድናቆታቸውን የገለጹት አሚሩ፤ የሁለትዮሽ ግንኙነቱ የበለጠ እንዲጠናከር ኩዌት ፍላጐት እንዳላት አስረድተዋል።

ዶክተር ወርቅነህ ከኩዌት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ አል ካህሊድ አል አህመድ አል ሳባህ ጋር በተመሳሳይ በሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ተነጋግረዋል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ