አርዕስተ ዜና

ኢትዮጵያ በጅቡቲና ኤርትራ ድንበር የተከሰተውን ውጥረት አገሮቹ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱት ጥሪ አቀረበች Featured

18 Jun 2017
959 times

አዲስ አበባ ሰኔ 11/2009 ኢትዮጵያ  በጅቡቲና ኤርትራ ድንበር መካከል የቆየው የኳታር ሰላም አስከባሪ ኃይል ከቦታው በመልቀቁ ምክንያት የተከሰተውን ውጥረት አገሮች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ለኢዜአ በላከው የፕሬስ መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ኢትዮጵያ ኳታር የሰላም አስከባሪ ወታደሮቿን ከጅቡቲና ኤርትራ ድንበር ካስለቀቀች በኋላ በአገሮቹ መካከል የተከሰተውን ውጥረት በቅርበት እየተከታተለች ነው።

ኢትዮጵያ ትናንት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት፤ በአገራቱ መካከል የተከሰተውን ውዝግብ ለመፍታት ጉዳዩን የሚያጣራ እውነታን ፈላጊ ልዑክ እንዲሰማራ ያቀረቡትን ሀሳብ እንደምትደግፍ መግለጫው አስታውቋል።

አገራቱ የተነሳውን ውዝግብ ከማባባስ ተቆጥበው ያላቸውን ልዩነቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ እንደምትፈልግ የጠቆመው የቃል አቀባዩ መግለጫ፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውጥረቱን ለማርገብ የሚያደርገውን ድጋፍ እንደምታበረታታ አትቷል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ