አርዕስተ ዜና

በናይል ተፋሰስ አገራት የውሃ ሀብት አጠቃቀም ላይ ያተኮረ ስብሰባ በመጪው ረቡዕ በኡጋንዳ ሊካሄድ ነው Featured

18 Jun 2017
666 times

አዲስ አባባ ሰኔ 11/2009 የተፋሰሱ አገራት መሪዎች በኢንቴቤ ስምምነት በልዩነት የወጡባቸው ሃሳቦችን ለመፍታት በመጭው ረቡዕ እንደሚወያዩ ሱዳን ትሪቢዩን ዘግቧል። 

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጣጠር በ2010 ይፋ የሆነው የኢንቴቤ ስምምነት የናይል ተፋሰስ አገራት የተፋሰሱን የውሃ ሀብቶች በጋራ የማስተዳደርና የማልማት መብት፣ኃላፊነትና ግዴታ እንዳለባቸው የሚያስቀምጥ የህግ ማዕቀፍ ነው። 

ስምምነቱ ኢትዮጵያ፣ኬንያ፣ኡጋንዳ፣ሩዋንዳና ታንዛንያ ስምምነቱን የፈረሙ ሲሆን የናይልን ወንዝ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ በጋራ ለመጠቀም የሚያስችላቸው ነው። 

አብዛኛውን የናይል ወንዝ ግብፅና ሱዳን እንዲጠቀሙ የሚያደርገውን የቅኝ ግዛት ዘመን ውል የተካ ነበር። 

የኢንቴቤ ስምምነት እየተባለ የሚጠራው ውል ቅኝ ገዢ በነበረችው ታላቋ ብሪታኒያ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1929 የተረቀቀና በናይል ወንዝ አጠቃቀም ላይ ከተፋሰስ አገሮች ይልቅ ለግብፅ ሙሉ መብት የሚሰጠውን ስምምነት የተካ ነው። 

ግብጽና ሱዳን ስምምነቱ የናይል ወንዝ አጠቃቀም ላይ እና ሌሎች ተጓዳኝ ጉዳዮች ላይ ተጽእኖ የሚያሳድር በሚል በወቅቱ ቅሬታቸውን አቅርበው ነበር። 

ነገር ግን ሁለቱ አገራት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2015 በሱዳን ርዕሰ መዲና ካርቱም በተካሄደው የናይል ተፋሰስ አገራት ስብሰባ በድጋሚ  መሳተፍ ጀምረዋል። 

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ