አርዕስተ ዜና

ኢትዮጵያና ኳታር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ Featured

19 May 2017
691 times

ግንቦት 11/2009 ኢትዮጵያና ኳታር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ማጠናከርና በጋራ ጉዳዮቻቸው ዙሪያ በትብብር መስራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡

የኢፌዲሪ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ ሚኒስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ በኳታር የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ በጉብኝታቸውም ከሃገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አህመድ ቢን አብዱላህ ቢን ዛይድ አል ማህሙድ ጋር የሁለቱ ሃገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ በሚጠናከርበት ዙሪያ መክረዋል፡፡

ባለስልጣናቱ በዶሃ ባደረጉት በዚሁ ምክክር ሃገራቱ ንግድና ኢንቨስትመንትን ጨምሮ በሁሉም ዘርፍ ግንኙነታቸውን ማሳደግ በሚችሉበት ዙሪያ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡ በተለይም ሁለቱ ሃገራት በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የበለጠ ማሳደግ እንደተጠበቀ ሆኖ በሚያስሟሟቸው በዓለም አቀፍና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

ገልፍ ታይምስ እንደዘገበው በውይይቱ ላይ በኳታር የኢትዮጵያ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋና የኳታር ካቢኔ ጉዳዮች ጄኔራል ሴክሬታሪያት ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተዋል፡፡

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ