አርዕስተ ዜና

ማህበራት እንዲጠናከሩ መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው Featured

21 Apr 2017
548 times

አዲስ አበባ ሚያዝያ 13/2009 የሙያ ማህበራትና የሲቪክ ተቋማት እንዲጠናከሩ "መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው" ሲሉ አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳ ገለጹ።

አገር አቀፉ የሲቪክ ማህበራት የምክክር መድረክ ዛሬ በሸራተን ተጀምሯል።

በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ እንዳሉት፤ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የሲቪክ ማህበራት፣ በየደረጃው ያሉ የህዝብ አደረጃጀቶችና የሙያ ማህበራት ጉልህ ድርሻ አላቸው።

በመሆኑም አገሪቷ የጀመረችውን የልማት፣ የመልካም አስተዳደር፣ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ለማሳደግ "በማህበራቱ ላይ ትኩረት በመስጠት እየሰራን እንገኛለን" ብለዋል፡፡

የሲቪክ ማህበራት በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ውስጥ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ሁሉ ሌሎች የሙያና ህዝባዊ ማህበራትም አብረው እንዲሰሩ ድጋፍና ክትትል ይደረጋል።

የብዙሃን ማህበራትም ዜጎችን በመብትና በጥቅማቸው ዙሪያ እየተወያዩ፣ እየተከራከሩ መሪዎቻቸውን እየሾሙና እየሻሩ፣ ዴሞክራሲውን የሚመሩባቸው መድረኮች እንደሆኑ ነው የገለጹት።

በመሆኑም መንግስት የሚያወጣቸው ፖሊሲና ህጎችን ተከትለው ከመብትና ጥቅም አኳያ እየተወያዩ የሚሻሻሉትን በማሻሻል፣ መቀጠል ያለባቸውን በማስቀጠልና በማስተካከል ተለይተው እንዲወጡ ይደረጋል።

ለሌሎች አካላት መብትም እንዲከራከሩ ሰፊ ዕድል ይሰጣቸዋል።

እነዚህ ማህበራት በዴሞክራሲያዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ሲሆን፤ ይህም ለዴሞክራሲያዊ ግንባታ ወሳኝ ድርሻ አለው።

መንግስትም ይህን አደረጃጀት ለማጠናከርና በንቃት እንዲሳተፉ ለማድረግ የተለያዩ ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠረ እንደሚገኝም አፈ ጉባኤ አባዱላ ተናግረዋል።

በዚህ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ዜጎች ከፖለቲካ አደረጃጀት ባሻገር በዕድሜ፣ በጾታ፣ በሙያና በማህበራዊ ግንኙነት ተደራጅተው በመታገል የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡም አሳስበዋል።

መንግስት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የጀመረው የምክክር፣ የክርክርና የውይይት መድረክ ለሙያ ማህበራት ትኩረት የሰጠ እንደሆነ የሚያሳይ  ነው።

መንግስት የሲቪክ ማህበራት ለአገራዊ ልማት፣ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች በቀጣይ ለሚካሄዱ ምክክሮችና ውይይቶች መሰረት የሚጥል መሆኑ ነው የተመለከተው።

በዛሬው አገር አቀፍ የምክክር መድረክ "ለአገሪቷ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የሲቪክ ማህበራት ተሞክሮዎች፣ ተግዳሮቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች" በሚሉ በምሁራን፣ በመንግስት፣ በሲቪክ ማህበራትና በህዝባዊ ተቋማት አራት ሰነዶች ይቀርባሉ ተብሏል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ