አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

ዴንማርክ በሳዑዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ድጋፍ ታደርጋለች Featured

20 Apr 2017
519 times

አዲስ አበባ ሚያዝያ 12/2009 ዴንማርክ የኢትዮጵያ መንግስት በሳዑዲ ዓረቢያ የሚኖሩ ዜጎቹን ወደ አገራቸው ለመመለስ የጀመረውን ተግባር እንደምትደግፍ ገለጸች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ የዴንማርክ የስደተኞች ኢንተግሬሽንና ቤቶች ሚኒስትር ሚስ ኢንገር ስቶይበርግን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሚኒስትር ዴኤታዋ ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገራት የሚመጡ ስደተኞችን በመቀበል እያስተናገደች መሆኑን ገልጸውላቸዋል።

ስደተኞቹን ከማስጠለልና አስፈላጊውን ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር በትምህርት ተቋማት ገብተው እንዲማሩ እያደረገች መሆኑንም እንዲሁ።

የአውሮፓ ኅብረትና አፍሪካ የጋራ የስደተኞች አጀንዳ ፕሮግራምና ሌሎች የትብብር ማዕቀፎችን ተፈጻሚ በማድረግ አገራቱ በስደተኞች ጉዳይ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር እንደሚችሉም አስረድተዋል።

ዴንማርክ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ስደተኞች እያደረገች ላለችው ድጋፍ አመስግነው ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።           

የዴንማርክ የስደተኞች ኢንተግሬሽንና ቤቶች ሚኒስትር ሚስ ኢንገር ስቶይበርግ በበኩላቸው አገራቸው የኢትዮጵያ መንግስት በሳዑዲ ዓረቢያ የሚኖሩ ዜጎቹን ወደ አገራቸው ለመመለስ እያከናወነ ላለው ተግባር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምታደርግ አረጋግጠዋል።

ከሳዑዲ የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን ከህብረተሰቡ ጋር ተቀላቅለው ማህበራዊ ኑሯቸውን እንዲቀጥሉ ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል ሚስ ኢንገር።

ትናንት በሰሜኑ የአገሪቷ ክፍል የሚገኝ የስደተኞች መጠለያ መጎብኘታቸውን ጠቅሰው ይህም የስደተኞችን አያያዝና እንክብካቤ ለማወቅ እንደረዳቸው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ለስደተኞች የምታደርገውን ድጋፍ ያደነቁ ሲሆን ዴንማርክ በቀጣይ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል።

ሁለቱ አገራት በኃይል አቅርቦት፣ በግብርና፣ በሰብዓዊ መብት ጉዳዮችና በቤት ውስጥ ፆታዊ ጥቃት መከላከል ላይ በቅርበት ይሰራሉ።

ዴንማርክ በዓለም አቀፉ የልማት ትብብር ኤጀንሲዋ ዲ.ኤ.ኤን.አይ.ዲ.ኤ አማካኝነትም ለኢትዮጵያ ድጋፍ ታደርጋለች።

ኢትዮጵያና ዴንማርክ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1960 ነው።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ