አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

አየር መንገዱ የሚጠቀመው ቴክኖሎጂ ተቋሙ የደረሰበትን የእድገት ደረጃ የሚያሳይ ነው- ፕሬዝዳንት ጌሌ Featured

18 Mar 2017
393 times

አዲስ አበባ መጋቢት 9/2009 የኢትዮጵያ አየር መንገድ እየተጠቀመበት ያለው ቴክኖሎጂ ተቋሙ የደረሰበትን የዕድገት ደረጃ የሚያሳይ ነው ሲሉ የጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማዔል ኦማር ጌሌ ተናገሩ።

ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት በዛሬው ዕለት አየር መንገዱ አብራሪዎችን የሚያሰለጥንበትን ምስለ-በረራ ከጎበኙ በኋላ ነው።

ምስለ-በረራውን የጎበኙት ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ፣ በመጀመሪያ ጉብኝታቸው ወቅት የነበረው በቦይንግ 767 የተመሰለ ሲሆን አሁን ያለው የድሪምላይነር መሆኑን ታዝበዋል።

ይህ ደግሞ አየር መንገዱ ምን ያህል ከቴክኖሎጂ እኩል እየተራመደ ራሱን እያዘመነ እንዳለ የሚያሳይ ነው ብለዋል።

'' አየር መንገዱ በየጊዜው ከፍ እያለ የአፍሪካን የአየር ትራንስፖርት ዘርፍ በቀዳሚነት እየመራ ነው ማለት ይቻላል'' በማለት እየተመራበት ያለውንም ሂደት አድንቀዋል።

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም በበኩላቸው አየር መንገዱ ራሱን በቴክኖሎጂ እያበቃ ለሌሎች ወዳጅ አገራትም የሚቻለውን ለማድረግ ዝግጁ ነው ብለዋል።

በርካታ የአፍሪካ አገራት በምስለ-በረራው ፓይለቶቻቸውን እያሰለጠኑ መሆኑን ዋና ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።

ጅቡቲም እየመሰረተች ላለው አዲስ አየር መንገድ ይህንን ቴክኖሎጂ ተጠቅማ ፓይለቶቿን ለማሰልጠን ፍላጎት ያለት በመሆኑ ቅድሚያ በመስጠት አብሮ ለመስራት ከስምምነት መደረሱን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ላይ የነበሩት የጅቡቲ ፕሬዝዳንት እስማዔል ኦማር ጊሌ በዛሬው ዕለት የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክንም ጎብኝተዋል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ