አርዕስተ ዜና

ሚኒስትሩ በሙኒኩ የጸጥታ ጉባኤ ለመሳተፍ ጀርመን ገቡ Featured

17 Feb 2017
458 times

የካቲት 10/2009 የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ዛሬ በሚጀምረው በ53ኛው የሙኒክ ፀጥታ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ጀርመን ገቡ።

ለሶስት ቀናት የሚቆየው የሙኒኩ የጸጥታ ጉባኤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስጋት በሆኑት ሽብርተኝነትና አክራሪነት እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ መክሮ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በሌላ በኩልም ስደትንና በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በተለይም በሶሪያ ያለው የእርስ በእርስ ግጭት እንዲሁም ዓለም አቀፍ የፀጥታ ችግሮች በጋራ ትብብር መፍታት በሚቻልበት ዙሪያም ጉባኤው ይመክራል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ