አርዕስተ ዜና

ናይጄሪያውያን በቦኮ ሃራም የተጠለፉ ልጃገረዶች እንዲመለሱ ግፊት እያደረጉ ነው

11 Jan 2017
565 times

ጥር 3/2009 ናይጄራውያን ከ1ሺ ቀን በፊት በቦኮ ሃራም የተጠለፉት  ተማሪ ልጃገረዶች እንዲመለሱ ግፊት እያደረጉ መሆኑን ሮይተርስ ዘገበ፡፡

ከተጠለፉት መካከል 24ቱ በህይወት ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለሳቸውንና ቀሪዎቹም  በህይወት አሉ የሚል ተስፋ እንዳሳደረባቸው ተገልጿል ፡፡

እንደፈረንጆች አቆጣጠር ሚያዚያ 2014 በሰሜን ናይጄሪያ ቺቦክ ከሚባል ቦታ በቦኮ ሃራም ታፍነው የተወሰዱት ልጃገረዶቹ  ከሁለት አመት በላይ ደብዛቸው ጠፍቶ እንደነበር የገለፀው ዘገባው ይህም አለም አቀፍ ቁጣን በመቀስቀስ “ልጆቻችንን መልሱ” የሚል ዘመቻ እንዲከፈት አድርጓል ይላል፡፡

ከተጠለፉት መካከል በግንቦት ወር አንዷ ወልዳ ከህፃኗ ጋር መገኘቷ፣ ሌሎች ሁለት ልጃገረዶች መገኘታቸውና በጥቅምት ወር በአለም አቀፉ ቀይ መስቀልና በስዊዘርላንድ አደራዳሪነት 21 ልጃገረዶች መለቀቃቸው ስለደንነታቸው ተስፋን እንደጫረም ተገልጿል ፡፡

ባለፈው ቅዳሜና እሁድ ልጃገረዶቹ የተጠለፉበት 1 ሺኛ ቀን ተዘክሮ ሲውል የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ሞሃመድ ቡሃሪ እንዳሉት የተጠለፉትን ልጃገረዶች ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመቀላቀል “የቻልነውን ሁሉ በአፋጣኝ እናደርጋለን ” ብለዋል፡፡

እኤአ በ2015 ወደ ስልጣን የመጡት ቡሃሪ ቀሪዎቹ ልጃገረዶች ሊመለሱ እንደሚችሉ ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል፤ ከሳቸው በፊት የነበረው የመንግስት አስተዳደር ልጃገረዶችን በማስመለስ በኩል በቂ ጥረት ባለማድረጉ ሲተች ቆይቷል፡፡

“እንባችን አልደረቀም ፣ህመሙም በልባችን ይሰማናል” ብለዋል ቡሃሪ፡፡

 

 

 

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ