አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

ግጭትን የመከላከሉ ስራ ለምርጫ የሚቀርብ ጉዳይ መሆን የለበትም … ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ Featured

11 Jan 2017
421 times

 ጥር 3/2009 በመላው ዓለም እየታየ ካለው የሰላምና ደህንነት ችግር አንጻር ግጭትን የመከላከሉ ስራ እንደ አማራጭ መወሰድ አይኖርበትም ሲሉ የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ተናገሩ ፡፡

ሚኒስትሩ “ግጭትን መከላከልና ሰላምን ማረጋገጥ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ  በሚኒስትሮች ደረጃ በኒዮርክ በተዘጋጀው   የክርክር መድረክ ላይ ንግግር አድርገዋል፡፡

የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ዋና ጸሃፊ ባንኪሙን በስራ ዘመናቸው ለዓለም ሰላም ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ያደነቁት ዶክተር ወርቅነህ፣ አዲሱ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝም ዓለም ላይ  ለሚስተዋሉ ግጭቶችና ስጋቶች አዳዲስ የመፍትሄ ግብዓቶችን እንደሚጨምሩ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትሩ አክለውም የአባል ሀገራቱ ድጋፍና ትብብር እስካልታከለበት ድረስ  የዋና ጸሃፊው ጥረት ብቻውን ፍሬያማ ሊሆን እንደማይችል አስገንዝበዋል፡፡

ኢትዮጵያ በግጭት መከላከል፣ አያያዝና በግጭት አፈታት ቁልፍ ሚና በመጫወት ላይ መሆኗን ያብራሩት ዶክተር ወርቅነህ፣ ሀገራቸው ለአዲሱ ዋና ጸሃፊ ያላትን አጋርነት አረጋግጠዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ብቻውን የሰላምና ጸጥታ ተግዳሮቶችን ሙሉ ለሙሉ ለመፍታት እንደማይቻለው አመልክተው፣ ከአህጉራዊና ክልላዊ አቻ ተቋማት ጋር ስትራቴጂያዊ አጋርነት መመስረት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘም ዋና ጸሃፊው በተባበሩት መንግሥታትና በአፍሪካ ህብረት ላለው አጋርነት ያሳዩትን ቁርጠኝነት አድንቀዋል፡፡

ፎረሙን በንግግር የከፈቱት የጸጥታው ምክር ቤት ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ግጭትን አስቀድሞ የመከላከል ስራዎች ላይ ተኩረት ሊደረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል-ግጭቶች በተፈጠሩ ጊዜ የሚሰጠውን ምላሽ ወደ መከላከሉ ማዞር የሚቻልበትን አዲስ አሰራር ማመቻቸት እንደሚገባ በመጠቆም፡፡

በክርክር መድረኩ ላይ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉተሬዝን ጨምሮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችና ሚኒስትር ዲኤታዎች እንዲሁም የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

 

ምንጭ፡- የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ