አርዕስተ ዜና

በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የደን ክልል የተነሳውን የእሳት ቃጠሎ መቆጣጠር ተቻለ

477 times

ጎንደር ሚያዚያ 5/2010 በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የደን ክልል የተነሳውን የእሳት ቃጠሎ መቆጣጠር መቻሉን የፓርኩ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የፓርኩ ከፍተኛ የቱሪዝም ባለሙያ አቶ አዛናው ከፍያለው ለኢዜአ እንደተናገሩት፥ የእሳት ቃጠሎው የደረሰው ትናንት ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ ነው፡፡

በጠለምት ወረዳ ልዩ ስማቸው ደንቆላኮና ምርቃ በተባለው የፓርኩ ደን ቦታ ላይ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ ለ14 ተከታታይ ሰዓታት ቆይቷል፡፡

የእሳት ቃጠሎው ወደ ሌሎች አካባቢ እንዳይዛመትና ሰፊ ጥፋት እንዳደርስ የወረዳው ህዝብና አመራሩ እንዲሁም የፓርኩ እስካውቶች ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ እሳቱን መቆጣጠር  ተችሏል፡፡

የቃጠሎው መንስኤ እስካሁን በውል አልታወቀም ያሉት አቶ አዛናው፥ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተም ፖሊስ እያጣራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ 

Rate this item
(0 votes)

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን