አርዕስተ ዜና

የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በምዕራብ ሀረርጌ ነዋሪዎች ተናገሩ

10 Jan 2018
266 times

ጭሮ ጥር 2/ 2010 ለአካባቢያቸው ልማት ምቹ ሁኔታ የፈጠረላቸውን የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በምዕራብ ሀረርጌ ዞን አስተያየታቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

በተያዘው ዓመት የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ በሀገር አቀፍ ደረጃ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ትናንት  በኦሮሚያ  ምዕራብ ሀረርጌ ዞን ገመቺስ ወረዳ ተጀምሯል፡፡

በስራው ላይ ከተሳተፉት የአካባቢው ነዋሪዎች መካከል አቶ ያሲን አሊዩ ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች ያገገሙ ተፋሰሶች ላይ የተለያየ ልማት ለማከናወን ምቹ ሁኔታ እንደተፈጠረላቸው ተናግረዋል፡፡

በጉዳት ምክንያት ተራቆቶ የነበረው አካባቢያቸው ከቅርብ ዓመታት ወዲህ  በተከናወነው የተፋሰስ ልማት መልሶ በማገገሙ የሚያጥማቸው የጎርፍ ችግር እንደቀነሰላቸውና የተለያዩ ምርት በማምረት ገቢ ማግኘታቸውን አቶ ያሲን አስታውቀዋል ፡፡

ያገገሙ ተፋሰሶች በበጋው ወቅት ወንዞችና ምንጮች የውሃ አቅማቸው እንዲጎለብት በማድረጋቸው ለመስኖ ልማት እንደጠቀማቸው የተናገሩት ደግሞ አቶ ሱፍ ኡመሬ የተባሉት የአካባቢው ነዋሪ ናቸው፡፡

በዚህም በመስኖ  ሽንኩርት ፣ድንች ጥቅል ጎመንና ቲማቲም በማልማት ለገበያ እያቀረበ ከሽያጩ በሚያገኙት ገቢ የራሳቸውንና  የቤተሰቦቻቸውን  ህይወት እየቀየሩ መሆናቸውንም አመልክተዋል፡፡

ተጠቃሚነታቸውን ለማጎልበት የጀመሩትን የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ነዋሪዎቹ ጨምረው  ተናግረዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ግብርና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ዱጉማ በበኩላቸው  ከዚህ ቀደም በድርቅ ተጎድተው የነበሩ ቦታዎች ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች  በማገገማቸው ለገጠሩ ወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

በክልሉ የዘንድሮው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ በ3ሺህ 245 ተፋሰሶች ላይ መጀሩን በዚህም አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ  ሄክታር መሬት የሚሸፈን መሬት ስራ እንደሚከናወን አቶ ደሳለኝ  አመልክታል፡

የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር ዶክተር ኢያሱ አብረሃ ገለጻ ዘንድሮ ለየት ባለ መልኩ የአፈርና ውሃ ጥበቃን ስራ ዘላቂና ጥራት ባለው ሁኔታ እንዲከናወን  በቂ ዝግጅት ተደርጎ  ወደ ስራ ተገብቶል፡

በተያዘው ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለአንድ ወር በሚከናወነው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ላይ ከ12 ሚሊዮን ሰዎች እንደሚሳተፉም ይጠበቃል፡፡

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ