አርዕስተ ዜና

የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የተጀመረው የደን ልማት ፕሮጀከት ውጤታማ መሆኑ ተገለጸ

18 Nov 2017
1478 times

ማይጨው ህዳር 9/2010 የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በትግራይ ደቡባዊ ዞን አምባላጌ  ወረዳ በፕሮጀክት ደረጃ የተጀመረው የደን ልማት ጥበቃ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ፡፡

ፕሮጀክቱ የተጀመረው ከአምስት ዓመት በፊት በሙከራ ደረጃ ነው፡፡

የወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጉዑሽ ሃይሉ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ፕሮጀክቱ በወረዳው በአራት የገጠር ቀበሌዎች በአንድ ሺህ200 ሄክታር መሬት  በመከለል ከሰውና ከእንስሳ ንኪኪ ነጻ በማድረግ ተጀምሯዋል።

ፕሮጀክቱ ሲጀመር  በተከለሉ ቦታዎች የነበረው የደን ሽፋን  ከአራት በመቶ በታች ነበር።

"ቦታዎቹ ከሰውና እንስሳት ንኪኪ ነፃ ከማድረግ ባለፈ  አንድ ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ችግኞችን እንዲተከሉ ማድረግ በመቻሉ አሁን የደን ሽፋኑን ከ12 በመቶ በላይ ሆኗል" ብለዋል፡፡

የአካባቢው ማህበረሰብ  ከደን ልማቱ የካርቦን ሽያጭ ተጠቃሚ ለማድረግ   የመረጃ ማሰባሰብና ጥናት ከመቀሌ ዩኒቨርሰቲ ጋር እየተከናወነ  መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

ፕሮጀክቱ የአካባቢው የመሬት ለምነትን በማሻሻል ምርታማነትን ከማሳደግ አልፎ አርሶአደሩ የመስኖ ልማት ተጠቃሚ እንዲሆን ያስቻለ መሆኑን ዋና አስተዳዳሪው ገልፀዋል፡፡

የደን ሽፋኑ እያደገ በመምጣቱ በማህበር የተደራጁ 12 ወጣቶች በንብ ማነብና የበጎች እርባታ ስራ መጀመራቸው  የተናገረው ደግሞ  የወረዳው ነዋሪ ወጣት ረዳኢ በርሀ ነው፡፡

"ከ2004 ጀምሮ በደን ልማቱ እየተጠቀምን ነው፤በማህበር ተደራጅተን የንብ ማነብ እያካሄድን እንገኛለን፤የወረዳው አስተዳደርና ኤስ ኤል ኤም የተባለ ድርጅት እያገዙን ተጠቅመናል"ብሏል

በተለይ በተፈጥሮ ደኑ ውስጥ ባለው የምንጭ ውሃ በመጠቀም የጌሾ ተክልን በማልማት ከምርቱ ሽያጭ እስከ 100 ሺህ ብር የሚደርስ ገቢ እያገኙ መሆናቸውን ወጣት ተናግራል፡፡

በደኑ ክልል የተቦረቦሩ ስፍራዎችን በመመለስ የጌሾ ተክልን በመስኖ እያለማና የበግ እርባታ በማካሄድ ጥቅም እያገኘ መሆኑን የገለጸው  ደግሞ የወረዳው ነዋሪ ወጣት ኪሮስ ከበደ ነው፡፡

"በደኑ ክልል ውስጥ የተቦረቦ መሬት የድንጋይና የአፈር  እርከን ሰርተን ለጌሾ ልማት እየተጠቀምን ነው፤ከጌሾ ልማት በተጓዳኝ  ሳር አጭደን በመሸጥ ያገኘነው ገቢ በጎችን ገዝተን በማርባት እየተጠቀምን ነው" ብሏል፡፡

 

 

 

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ