አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

የዘንድሮው ውርጭ ጉዳት እንደማያደርስ ተገለጸ

04 Nov 2017
1881 times

አዲስ አበባ ጥቅምት 25/2010 የዘንድሮው ውርጭ እንደአምናው በእንስሳትና እፀዋት ላይ ጉዳት እንደማያደርስ የብሔራዊ ሚትዮሮሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ።

በበጋ ወቅት በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ ተጽኖ ከሚያደሱ የአየር ጸባይ ለውጦች መካከል በትሮፒካል የፓስፊክ ውቅያኖስ የመካከለኛውና የምስራቃዊው ክፍል ከመደበኛ በላይ ሲሞቅ የሚከሰት ድርቅና ከመደበኛው በታች በመቀዝቀዝ የሚፈጠር ከፍተኛ ውርጭ ነው።

በአገሪቱ ሰሜን አካባቢዎች አዲግራት፣አክሱም፣ ደብረብረሃንና ወገል ጤና፤ ፍቼ እና ገብረ ጉራቻ እንዲሁም በምስራቅ የአገሪቱ ክፍል ሀረርና ሀሮማያ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ለውርጭ የሚጋለጡ አካባቢዎች መሆናቸውን የኤጀንሲው መረጃ ያሳያል።

ባለፈው ዓመት በእነዚህ አካባቢዎች በተከሰተ ከፍተኛ ውርጭ በሰው፣በእንስሳትና በዕጽዋት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፣በተለይ በሀሮማያ ወረዳ በሚገኙ 14 ቀበሌዎች ከሁለት ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ የተዘራ የአትክልትና የጫት ሰብል ሙሉ ለሙሉ መውደሙ ይታወቃል።

የኤጀንሲው የሚትዮሮሎጂ ትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ዳይሬክተር ተወካይ አቶ አሳምነው ተሾመ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በዘንድሮው የበጋ ወቅት ለጠንካራ ውርጭ መፈጠር  አመች የሆኑ ክስተቶች  እስካሁን አልታዩም።

በዚህም በዘንድሮው ዓመት ከባድ ውርጭ ባይከሰትም የተለመደና መጠነኛ ውርጭ ሊኖር እንደሚችል ገልጸዋል።

በአጠቃላይ ሲታይ በበጋው ወራት ከመስከረም መጨረሻ አካባቢ ጀምሮ  ደረቅ፣ፀሃያማ፣ጠንካራ ንፋስ እንዲሁም በማለዳና በምሽት ቅዝቃዜ የሚስተዋልበት ጊዜ ይሆናል ነው ያሉት።

በበጋው ወቅት የደቡብ፣ደቡብ ምዕራብና የደቡብ ምስራቅ የአገሪቱ አካባቢዎች በአማካኝ ከ200 እስከ 450 ሚሊ ሜትር ዝናብ እንደሚያገኙም ገልጸዋል።

በአንጻሩ የአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍልን ጨምሮ የመካከለኛውና ምስራቅ አካባቢዎች በአመዛኙ ከአንድ መቶ ሚሊ ሜትር የማይበልጥ ዝናብ እንደሚኖራቸው አቶ አሳምነው ተናግረዋል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ