አርዕስተ ዜና

የአካባቢ ቁጥጥር ስራ በማከናወናችን የወባ በሽታን ለመከላከል ረድቶናል- የምሰራቅ ጎጃም ዞን ነዋሪዎች

09 Oct 2017
1896 times

ደብረ ማርቆስ 29/1/2010 በልማት ቡድናቸው አማካኝነት ባካሄዱት የወባ መከላከልና ቁጥጥር ስራ ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ከበሽታው መጠበቅ እንዳስቻላቸው በምስራቅ ጎጃም ዞን አስተያየታቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ገለፁ።

የክረምቱን መውጣት ተከትሎ የወባ ወረርሽኝ እንዳይከሰት ህብረተሰቡን ያሳተፈ የቅድመ መከላከል ስራ መካሄዱን የዞኑ ጤና መምሪያ አስታውቋል።

አስተያየታቸውን ከሰጡ መካከል የባሶሊበን ወረዳ የነተመን ቀበሌ ነዋሪ አቶ ፈንታሁን አጥናፉ ቀደም ሲል በክረምቱ መውጫ የአካባቢው ነዋሪ በወባ ስለሚጠቃ በልማት ስራ ላይ ጫና ይፈጠራል።

በጤና ባለሙያዎች በተሰጠ የምክር አገልድሎት በየአመቱ ከመስከረም ወር መግቢያ ጀምሮ ለትንኝ መራቢያ  አመቹ  የሆኑ ውሀ የሚያቆሩ ረግረጋማ ቦታዎችን የማዳፈንና ሌሎች ተጓዳኝ ስራዎችን በዘመቻ በመስራታቸው የበሽታው ጥቃት እየቀነሰ መምጣቱን ተናግረዋል።

"ባለፉት አመታት በበሽታው ባለመያዜ በግልም ሆነ በአካባቢው የልማት ስራ ሳልሳተፍ የቀረሁበት ጊዜ የለም" ብለዋል።

ዘንድሮም ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር በመሆን ውኃ ያቆሩ ቦታዎችን   የማፋሰስ፣ የማዳረቅና በአካባቢ ፅዳት መሳተፋቸውን ተናግረዋል።

የደብረ ኤልያስ ወረዳ የዱግ ቀበሌ ነዋሪ ወይዘሮ  አለሚቱ ተሾመ በበኩላቸው ቀደም ሲል እስከ ህዳር ወር እራሳቸውና ቤተሰባቸው በወባ በሽታ በመታመም ወደ ህክምና ተቋም የሚመላለሱበት ጊዜ እንደሚበዛ አስታውሰዋል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአካባቢያቸው የተመደቡ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች የሚሰጡዋቸውን የምክር አገልግሎት ተቀብለው  የቅደመ መከላከል ሰራ በመስራታቸው ከበሽታው መጠበቃቸውን ገልፀዋል።

የወባዉ ትንኝ መከላከያ የአልጋ አጎበር በአግባቡ በመጠቀማችን በበሽታው እንዳንያዝ የበለጠ ረድቶናል" ብለዋል።

ከዚህ በፊት የቤተሰቡ አባላት በበሽታው ተይዞ ይባክን የነበረው የስራ ጊዜና ገንዘብ እየቀረ መምጣቱን ተናግረዋል።

የክረምቱን መውጣት ተከትሎ በአካባቢው የወባ በሽታ እንዳይከሰት አስቀድሞ ለመከላከል በልማት ቡድናቸው አማካኝነት የጽዳት ዘመቻ  በማካሄድ ላይ መሆናቸውን የገለፁት ደግሞ የአነደድ ወረዳ የጽድ ማሪያም ቀበሌ ነዋሪ አቶ መኳንንት ልጃለም ናቸው።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ የወባና መሰል በሽታዎች መከላከል የስራ ሂደት አስተባበሪ አቶ ንብረት በሪሁን እንደተናገሩት በክረምቱ መውጣት ጋር ተያይዞ ሊከሰት የሚችለውን የወባ ወረርሽኝ ለመከላከል ህብረተሰቡን ያሳተፈ የቅድመ መከላከል ስራ እየተካሄደ ነው፡፡

ከነሀሴ ወር 2009 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ ከ100 ሺህ በላይ ህዝብ በማሳተፍ ችግሩ በስፋት በሚታይባቸው 13 ወረዳዎች በ192 ሄክታር ረግረጋማ መሬት ላይ የተኛዉን ውሀ የማፋሰስና የማዳረቅ ስራ መከናወኑን ለአብነት ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም የጨፌና ሳር አጨዳና የአካባቢ ፅዳት ስራ መሰራቱን አስረድተዋል።

"ለበሽታው ተጋላጭ በሆኑ 18 ወረዳዎች ከ120 ሺህ በላይ ቤቶች ላይ የፀረ ወባ ትንኝ ኬሚካል ርጭት ተካሄዷል"ብለዋል።

እንደ አስተባባሪው ገለፃ የዞኑ ህብረተሰብ እስካሁን ባለው የቅድመ መከላከል ሂደት 8 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር የሚገነት የጉልበት አሰተዋፆ አበርክቷል።

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ