አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

የትምህርት ተቋማት በአካባቢ ጥበቃ ስራ ላይ በትኩረት ሊሳተፉ ይገባል--- የመምህራን ማህበር

07 Oct 2017
2228 times

ሶዶ መስከረም 27/2010 በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል የሚገኙ የትምህርት ተቋማት ከመማር ማስተማሩ ባሻገር በአካባቢ ጥበቃ ስራ ላይ በትኩረት ሊሳተፉ እንደሚገባ የክልል መምህራን ማህበር አሳሰበ፡፡

ማህበሩ " የተፈጥሮ ሃብታችን ለህዳሴያችን "በሚል መርህ ሀሳብ  በወላይታ ዞን ከሚገኙ የትምህርትና  ግብርና ባለሙያዎች ጋር ተወያይታል፡፡

የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ አማኑኤል ጳውሎስ በውይይቱ ወቅት እንደተናገሩት ማህበሩ የአባላትን መብትና ጥቅም ከማስጠበቅና ለትምህርት ጥራት ከመስራት በተጓዳኝ በተፈጥሮ ሃብት አያያዝና ጥበቃ ዘርፍም የድርሻውን ይወጣል፡፡

በክልሉ የሚንቀሳቀሱ "የትምህርት ተቋማትም ከመማር ማስተማር ስራ ባሻገር በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሳተፍ አለባቸው" ብለዋል፡፡

ትምህርት ቤቶች ክበባትን በማደራጀትና በማጠናከር ባላቸው የይዞታ መሬት ላይ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና ልማትን በማጠናከር ለአከባቢው ህብረተሰብ ምሳሌ  ሊሆኑ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በአከባቢያቸዉ የሚገኙ የተራቆቱና ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን በማልማትና የአከባቢውን ህብረተሰብ በማስተባበር ችግር ፈቺ ጥናቶች ማካሄድም ይጠበቅባቸዋል፡፡

ማህበሩም እስከታች ድረስ ባሉት መዋቅሮቹ የሚካሄዱ ተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራዎችን  እንደሚደግፍ አቶ አማኑኤል ተናግረዋል፡፡

የወላይታ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ዶክተር ጌታሁን ጋረደው በበኩላቸው  የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ተጽእኖ ለመከላከል ሰፊውን ማህበረሰብ የሚደርሱ የትምህርት ተቋማት ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በውይይቱ የቀረቡ የጥናት ውጤቶችን በዞኑ በሚገኙ ከ600 በላይ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

" የአካባቢ ጥበቃ ስራ ለአንድ ተቋም ብቻ የሚተው  ባለመሆኑ ማህበሩ ኃላፊነቱን ለመወጣት ሃሳቡን ይዞ መቅረቡ ተገቢ ነው " ያሉት ደግሞ የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ክፍሌ ታውሌ ናቸው፡፡

መምሪያው ለአከባቢው ስነ ምህዳር የሚስማሙና ምርትና ምርታማነትን የሚጨምሩ ችግኞችን በማቅረብ ከትምህርት ዘርፉ  ጋር እንደሚሰራ ጠቁመው ችግኞችን ለማፍላት ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ  መድቦ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

በውይይት መድረኩ  "በክልሉ ያሉ ዕምቅ የተፈጥሮ ሃብቶችን በተቀናጀ መልኩ መጠበቅ" በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርቦ  ምክክር ተደርጎባቸዋል፡፡

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የለማው የቡጌ ዋንቼ የተፋሰስ ልማት ስራም በተሳታፊዎች ተጎብኝቷል፡፡

የዞኑ ትምህርትና እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት መምሪያዎችም ለቀጣይ ስራቸው የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ