አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

የአፍሪካ ሀይድሮሜት ፎረም በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

08 Sep 2017
2227 times

አዲስ አበባ ጳጉሜ 2/2009 ሃይድሮ ሜት ተብለው ከሚታወቁት የአየር ሁኔታ ፣ ውሃ እና የአየር ንብረት አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ በሜቲዎሮሎጂ ላይ የሚመክር የሚኒስትሮች ጉባዔ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው፡፡

ጉባዔው የዓለም ባንክ ግሩፕ፣ የአፍሪካ ህብረት፣ የዓለም ሜቲዎሮሎጂ ድርጅት፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ፣ የፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ፣ የዓለም ምግብ ፕሮግራም እና የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ትብብር የተዘጋጀ ነው፡፡

በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት አዲስ አበባ ከመስከረም 02 ቀን 2010 ጀምሮ ለአራት ቀናት በሚካሄደው ጉባዔ የሃይድሮ ሜት ፎረም ይመሰረታልም ተብሏል፡፡

ተቋማቱ ባወጡት የጋራ መግለጫ እንደተገለጸው በዓይነቱ የመጀመሪያ በሆነው በዚህ ፎረም ከተፈጥሮ አደጋ ጋር የተያያዙ ጉዳቶችን ለመቀነስና ኢኮኖሚን ለማሳደግ እየሰሩ ያሉ የአፍሪካ መሪዎች፣ የመንግስትና የግል ዘርፍ፣ ከሲቪል ማህበረሰብና ከልማት አጋሮች የተውጣጡ 500 ልዑካን ይሳተፉበታል፡፡

በአፍሪካ እየደረሱ ካሉት 10 የተፈጥሮ አደጋዎች 9ኙ ከአየር ሁኔታና አየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ እንደሚከሰት የሚገልጸው መግለጫው ባለፉት ሃያ አመታት ብቻ አህጉሪቱን በጎርፍ፣ ድርቅ፣ የመሬት መንሸራተት እና አውሎ ንፋስ ከ10 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚበልጥ ሀብት አሳጥቷታል።

ፎረሙ በአፍሪካ ላለው ዘላቂ ልማት ለማስቀጠል ዘመናዊ የውሃና የአየር ፀባይ  መረጃ አያያዝ ላይ መግባባት ይፈጥራልም ተብሏል።

የአየር ንብረት ለውጥንና አደጋዎችን ለመቀነስ የውሃ ሃብት፣ሜትዮሮሎጂ እና ቅድመ-ማስጠንቀቂያ ስትራቴጂዎች ይቀርቡበታል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ