አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

በትግራይ ሰሜናዊ ዞን በህዝብ ተሳትፎ የተከናወነ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራ ውጤታማ ሆኗል

07 Sep 2017
2105 times

ሽሬ እንዳስላሴ ጳጉሜ 2/2009 በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት የተመናመነውን የተፈጥሮ ሃብት በህዝብ የነቃ ተሳትፎ መልሶ ለመተካት የተከናወነው ስራ ውጤታማ መሆኑ ተገለፀ፡፡

በዞኑ የአረንጓዴ ልማት ቀን ቀደም ሲል ለተተከሉ ችግኞች እንክብካቤ በማድረግ ትናንት ተከብሯል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ዘካርያስ ሽፈራው  በወቅቱ እንደገለፁት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት ባለፉት ዓመታት በህዝብ ተሳትፎ በተካሄደ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ተራቁቶ የነበረ አካባቢ መልሶ እንዲያገግም አስችሏል፡፡

ይህም የአካባቢው  ልምላሚ እንዲመለስና የመስኖ ልማት እንዲስፋፋ አስተዋዕኦ አበርክቷል።

በዚህም ከአስር ዓመት በፊት በዞኑ በመስኖ ይለማ የነበረው ከ20 ሺህ ሄክታር የማይበልጥ መሬት በአሁኑ ጊዜ ከ70 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ማልማት ተችሏል።

የዞኑ የተፈጥሮ ኃብት እንክብካቤ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ አብራሃም ሙሉ በበኩላቸው "ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት የተያዘውን ግብ ለማሳካት በየአካባቢው የተጀመረው የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ ይበልጥ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል" ብለዋል፡፡

ደንን መትከል ብቻ ሳይሆን በመንከባከብ የጽድቀት መጠኑን በመጨመር የአየር ለውጥን መግታትና የሚያስከትለውን የተፈጥሮ አደጋ መከላከል እንደሚገባም ገልፀዋል፡፡

“የአረንጓዴ ልማት ቀን በአገር ደረጃ መከበሩ በዘርፉ የተጀመረውን እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ለማስቀጠል ያግዛል ” ያሉት ደግሞ የሽሬ እንዳስላሴ እርሻ ኮሌጅ ዲን አቶ ተክላይ ገብረ ትንሳኤ ናቸው።

በዞኑ የሚገኙ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላትም የአረንጓዴ ልማት ቀንን ቀደም ሲል የተከሉዋቸውን ችግኞችን በመንከባከብ አክብረዋል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ