አርዕስተ ዜና

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን 261 ሚሊዮን ችግኝ ተዘጋጀ

17 May 2017
1139 times

ፍቼ ግንቦት 9/2009 በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በመጪው የክረምት ወራት የሚተከል 261 ሚሊዮን ችግኝ ተዘጋጀ፡፡

ችግኙ የተዘጋጀው በዞኑ በሚገኙ 2 ሺህ 292 የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች  ነው፡፡

የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት የደን ጥበቃና አጠቃቀም የስራ ሂደት ኃላፊ ወይዘሮ ሻሺቱ ባጫ ለኢዜአ እንደገለፁት ችግኙ በዞኑ 13 ወረዳዎች በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ሳቢያ በተራቆተ 51 ሺህ ሄክታር  መሬት  ላይ  ይተከላል፡፡

ለተከላ ከተዘጋጀው ችግኝ ውስጥ የሀበሻ ጥድ ፣ ባህር ዛፍ ፣ ግራር ፣ ዋንዛና የተለያየ የፍራፍሬ ችግኝ ይገኝበታል፡፡

የችግኝ ተከላውን ውጤታማ ለማድረግ በአርሶ አደሮች ተሳትፎ በአሁኑ ወቅት በየአካባቢው የጉድጓድ ቁፋሮ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል ።

ለችግኝ መትከያ ጉድጓድ  በማዘጋጀት ላይ ካሉት የደገም ወረዳ አርሶአደሮች መካከል  የቁንዴ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ጆቴ መርጋ በሰጡት አስተያየት የተፈጥሮ ሃብትን መንከባከብ ለእርሻ ስራቸው  የሚረዳ መሆኑን  በመገንዘባቸው ከወዲሁ ጉድጓድ በመቆፈር እርጥበት እንዳይባክን እያደረጉ መሆኑን ገልፀዋል።

የሚተክሉት ዛፍ ለእንስሳት መኖና ለማገዶ  የሚያወጡትን ወጪ ከመቀነስ በተጨማሪ የገቢ ምንጭ ሆኖ የሚያገለግል በመሆኑ በማሳቸው አካባቢ ችግኝ ለመትከል አስፈላጊው ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል ።

በዞኑ ባለፈው ዓመት ከተተከሉ  348 ሚሊዮን ችግኞች መካከል 78 በመቶ የሚሆነው መፅደቁ በቆጠራ ማረጋገጥ እንደተቻለ ከግብርና ፅህፈት ቤት የተገኘ መረጃዎች ያመላክታል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ