አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

በአማራ ክልል የጎርፍ አደጋን ለመከላከል የሚያስችል ስራ እየተከናወነ ነው

09 May 2017
1255 times

ባህር ዳር ግቦት1/2009 በአማራ ክልል በ30 ሚሊዮን ብር ወጪ በክረምት ወቅት ሊከሰት የሚችለውን የጎርፍ አደጋ ለመከላከል የሚያስችል ስራ መጀመሩን የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

 በፅህፈት ቤቱ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ባለሙያ አቶ ብርሃኑ ዘውዱ ዛሬ እንዳስታወቁት የጎርፍ መከላከል ስራው ካለፈው ወር አጋማሽ ጀምሮ በተመረጡ ቦታዎች እየተካሄደ ነው።

 የመከላከል ስራው የተጀመረው የጎርፍ አደጋ ተጠቂ ናቸው ተብለው በጥናት በተለዩ ሰሜን ሽዋ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች ውስጥ በሚገኙ አንፆኪያ፣ ቀዎት፣ አጣየ ፣ ደሴ፣ ቃሉ፣ ተውለደሬ፣ ሃይቅ ፣ ቆቦ፣ ሃብሩና መርሳ ከተሞች ነው።

 ከሚሰሩት ስራዎች መካከልም አቅጣጫቸውን ስተው የሚወጡ ወንዞችን ለመከላከል የጎርፍ መቀልበሻ ግድብና የመሬት መንሸራተትን ለመከላከል የሚያስችል የክትር ስራ ይገኙበታል።

 እንዲሁም የጎርፍ ማፋሰሻ ቦይ ግንባታ፣ የኮንክሪት ሙሊት፣ የአፈር ግድብ፣ የዲች ስራዎችና የወንዝ ደለል ጠረጋ እንደሚከናወኑ ተናግረዋል።

 የጎርፍ መከላካያ ስራው ከሰኔ 30 ቀን 2009 በፊት እንዲጠናቀቁ ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 የጎርፍ መከላከያ ስራው በሚካሄድባቸው አካባቢዎች 8 ሺህ 153 አባዎራዎችን፣ አምስት ሺህ 362 ሄክታር የሰብል ማሳ እንዲሁም ሁለት ትምህርት ቤቶችንና አንድ መስጊድ ከስጋት ለመጠበቅ እንደሚያስችል አብራርተዋል።

 ባለፈው ዓመትም በምዕራብ አማራ በሚገኙ የስጋት ቀጠናዎች የተለያዩ የግድብና የክትር ስራዎችን በማከናወን ህዝቡን ከአደጋ መጠበቅ እንደተቻለም አቶ ብርሃኑ ጨምረው ገልፀዋል።

 

 

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ