አርዕስተ ዜና

በምሥራቅ ወለጋ ዞን 287 ተፋሰሶችን መሰረት ያደረገ የተፈጥሮ ህብት ልማት ሥራ ሊካሄድ ነው

08 Jan 2017
923 times

ነቀምት ታህሳስ 30/2009 በምሥራቅ ወለጋ ዞን በተያዘው በጋ  287 ተፋሰሶችን መሰረት በማድረግ  143 ሺህ ሄክታር የተጎዳ መሬት ላይ የተፈጥሮ ህብት ልማት ሥራ  ለማካሄድ ዝግጅት መደረጉን  የዞኑ የእርሻና  የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡

ጥር 19/2009ዓ.ም  በሚጀመረው በዚሁ  የልማት ስራ ከ400  ሺህ በላይ አርሶ አደሮች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

በጽህፈት ቤቱ የተፈጥሮ ሀብት ልማት የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ብሩክ ጫላ ለኢዜአ እንደገለጹት በስራው  አፈጻጸም ዙሪያ መሪ ለሆኑ ግንባር ቀደም  ሞዴል አርሶ አደሮችና የግብርና ባለሙያዎች  የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።

ለልማቱ ማካሄጃ የሚሆኑ ቀላል የእጅ መሳሪያዎች መዘጋጀታቸውንም ጠቁመዋል ።

አስተባባሪው እንዳመለከቱት ከሚከናወኑት ስራዎች መካከል የእርከን ፣ የእርጥበት ማቆሪያ ጉድጓዶች ቁፋሮና  የተቦረቦሩ ቦታዎችን ማስተካከል ይገኙበታል፡፡

በተያዘው በጋ የሚካሄደው  የተፈጥሮ ሀብት ልማት በዞኑ የተጎዳን አካባቢ መልሶ እንዲያገግም ባለፉት ዓመታት ሲካሄድ የቆየውን ስራ ለማጠናከር መሆኑም ተመልክቷል፡፡

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ